ውክፔዲያ amwiki https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8C%88%E1%8C%BD MediaWiki 1.45.0-wmf.7 first-letter ፋይል ልዩ ውይይት አባል አባል ውይይት ውክፔዲያ ውክፔዲያ ውይይት ስዕል ስዕል ውይይት መልዕክት መልዕክት ውይይት መለጠፊያ መለጠፊያ ውይይት እርዳታ እርዳታ ውይይት መደብ መደብ ውይይት በር በር ውይይት TimedText TimedText talk Module Module talk Event Event talk እርዳታ:ይዞታ 12 804 385931 370412 2025-06-26T15:46:13Z 102.213.69.138 385931 wikitext text/x-wiki === ማንኛውንም ገጽ ስለ ማዘጋጀት ወይም ስለ ማስተካከል ሌላ ጠቃሚ መረጃ በ[[Help:Editing|ማዘጋጀት ዕርዳታ]]ው ገጽ ላይ ይገኛል። === ==<font size="+1">በፊደል ማቀነባበር በቀላሉ!== <font size="+1">ባማርኛ ለመጻፍ የተለያዩ ዘዴዎች አሉ። እነዚህን ዘዴዎች ከዚህ ቀጥሎ በመዘርዘር ምርጫውን ለተጠቃሚ እንተዋለን። ===<font size="+1">ራሱ ገጹ ላይ የተገጠመው ዘዴ</font >=== ==== <font size="+1">ኢትዮ ፒክ ሴራ ==== <font size="+1"> የፍለጋ ሳጥኑ (search box) ላይና የጽሁፍ ሳጥኑ (editbox) ላይ የተገጥመው የአማርኛ መጻፊያ እንዴት እንደሚሰራ [[ኢትዮፒክ ሴራ]] ላይ ስላለ እስለኪለመድ በራሱ መስኮት ላይ ከፍቶ እያዩ መጻፉ ይረዳል::ይህን ዘዴ ካልተጠቀሙ ሌሎች ዘዴዎች ከዚህ ቀጥሎ ተዘርዝረዋል። ===<font size="+1">በ ሲስተም ደረጃ የሚሰሩ የጽሁፍ ረዳት ሶፍትዌሮች (virtual keyboards)=== <font size="+1"> ==== <font size="+1">ግዕዝ ሀበነ ==== <font size="+1">ግዕዝ ሀበነ ማንኛውም ሶፍትዌር ላይ በግዕዝ ፊደሎች ለመጻፍ የሚያስችል ሶፍትዌር ነው። የሚሰራው MS/Windows ኮምፒውተሮች ላይ ሲሆን አጠቃቀሙ የተለየና የግዕዝ ፊደሎችን ድምጽ የተከተለ ነው። እዚህ ገጽ [http://www.branah.com/ethiopic www.branah.com] ላይ እንዴት ሶፍትዌሩን ማውረድና መጫን እንደሚቻል፣ አጠቃቀሙንም ጭምር የሚያሳይ ቪዲዮ ያገኛሉ። ==== <font size="+1">ፋየር ፎክስ እና አኒኪ ==== <font size="+1">ፋየር ፎክስን (Mozilla firefox) [http://www.mozilla.org/ firefox] የሚባለውን <font size="+1">የኢንተርኔት መጎብኛ (browser) ለምትጠቀሙ በፊደል የማዘጋጀት ዘዴ ተዘጋጅቷል። ከማዘጋጀት ሠንተረዡ በላይ «በፊደል ለመጻፍ - ...write in Amharic» ከሚለው አጠገብ ያለው ሣጥን ካለተመረጠ በቀር የሚጻፈው ሁሉ ቀጥታ በፊደል ይታያል። <font size="+1"> ከዚህ ሌላ [https://addons.mozilla.org/firefox/3990/ anykey] ላይ እራሱ ፋየር ፎክስን በመጠቀም የሚሠራ ጠቃሚ መጨመርያ አለ። እዚህ ቦታ ላይ በፋየር ፎክስ አማርኛን በመጠቀም ኢንተርኔት ላይ ለመጻፍ የሚያገለግል extension ይገኛል። የሰፈሩትን ጽሁፎች ከቃኙ በኋላ install now የሚለውን መያያዣ ይጫኑት። ይህ ዘዴ <font size="+1">ኢንተርኔት ላይ ፎርም፣ ብሎግ፣ ዌብ ሜልና የመሳሰሉትን (ዊኪፔዲያን ጨምሮ) በቀላሉ ባማርኛ ቀጥታ ለመጻፍ ያስችላል! (በፋየር ፎክስ ላይ View -> Character Encoding -> Unicode UTF-8) እንደ ተመረጠ ያረጋግጡ። በመጎበኛው ቀኝ-ታች ማዕዘን ላይ «አﻯки» ሲታይ ሁለት ጊዜ ይጫኑት፣ 'Keymaps' -> 'Ethiopic Sera' ይምረጡ። ከዚያ በኋላ በEdit box ውስጥ <F2> ወይም «right click» ተጭነው በፊደል በቀጥታ ማዘጋጀት ይቻላል!) ይህን ዘዴ የሚያስረዳ ፊልም ወይም ቪዲዮ ለማግኘት [http://www.youtube.com/watch?v=FtFplPQfXj0 እዚህ ይጫኑ] ====<font size="+1">washra - ዋሽራ==== <font size="+1">ዋሽራ ማንኛውም ሶፍትዌር ላይ ባማርኛ ለመጽፍ የሚረዳ ሰሌዳንና (keyboard) ፎንትን ያዘለ ሶፍትዌር ነው። እዚህ ገጽ ([http://www.senamirmir.com/projects/typography/washra.html washra]) ላይ የሚገኘውን ማስረጃ በጥሞና ማንበብና ሶፍትዌሩን መጫን በጣም ጠቃሚ ነው። ይህ ሶፍትዌር አጠቃቀሙን የሚያስረዱ ጽሁፎችን ስለሚይዝና የተለያዩ ፎንቶችን (የፊደል ቅርጾችን) ስለሚያስቀምጥ ሊሞከር የሚገባው እጅግ ጠቃሚ ሶፍትዌር ነው። (* ማስታወቂያ - ይህ ዘዴ ለ"Windows XP", "Windows 2000", እና ከዚያ በላይ ላላቸው ኮምፒዩተሮች እንጂ ከ"Windows ME" ጋራ አይስማማም።) ====Tavultsoft keyman==== <font size="+1">ባማርኛ በቃል ማቀነባበርያ ውስጥ ታይፕ ለማድረግ ከፈለጉ፣ በዚሁ በጣም ጠቃሚ ሥፍራ አለዋጋ ያገኙበታል http://www.abyssiniacybergateway.net/fidel/unicode/ በተለይም "Keyboards" በሚለው አርስት ሥር "Amharic" ያለው ፕሮግራም ይጠቅማል። ይህ ፕሮግራም በነጻ የሚስጥ ነው። ከዚያ በኋላ "Tavultesoft Keyman" የሚባል ፕሮግራም በኮምፒውተርዎ ላይ ያስቀምጣል። <font size="+1">እሱን ከፍተው በታችኛ ቀኝ ማዕዘን በኩል ከዚያ በሚገኘው ምልክት 1 ወይም 2 ጊዜ ተጭነው "Amharic Unicode EZ" የሚለውን ይምረጡ። ከዚያ የቃል ማቀነባበርያ ለምሳሌ እንደ "Wordpad" ከፍተው፣ "GF Zemen Unicode" በሚባል ፎንት ታይፕ ላማድረግ ቀላል ነው። በኮምፒውተርዎ ውስጥ በ C:\WINDOWS\All Users\Application Data\Tavultesoft\Keyman\Keyboard\unicode-ez\AmharicHelp.htm ወይም እንደዚያ በሚመስል ሥፍራ ያለው ሰነድ የፕሮግራሙ ታይፕ አሠራር በቀላሉ ያስረዳዎታል። ነገር ግን የፈለጉትን በ"Wordpad" ከጻፉ በኋላ እሱን ወደ ዊኪፔድያ ለማዘዋወር "cut"ና "paste" ማድረግ ያስፈልጋል። <font size="+1">windows xp እና internet explorer 6 ለምትጠቀሙ ይህ "Tavultesoft Keyman" የተሰኘው ፕሮራምን በመጠቀም ግን በቀጥታ ድረ ገጽ ላይ በመሄድ ለመጻፍ ይቻላል። ይህን ዘዴ የሚያስረዳ ቪዲዮ [http://www.youtube.com/watch?v=5oOWStEQz4g&feature=related እዚህ ይመልከቱ] ===<font size="+1">Unigeez=== <font size="+1">ከዚሁ ጋር ተመሳሳይ የሆነውን unigeez የሚሰኘውን ፕሮግራም ከመረጡ [ftp://ftp.ethiopic.org/pub/UniGeez/ unigeez] ላይ ያገኙታል። ===<font size="+1">ጃቫ (java)=== <font size="+1">ሌላ የአማርኛ መጻፊያ ፕሮግራም እዚህ ይገኛል [http://senamirmir.com/projects/sadiss/sadiss_proj/sadiss.html sadiss]. ጃቫ የሚሰኘውን የኮምፒውትር ቋንቋ የሚጠይቅና በሱም የተሰራ ስለሆን ኮምፒውተሩ ላይ ለመጫን በቅድሚያ [http://java.sun.com/j2se/1.4/download.html java] ላይ መሄዱ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። <font size="+1">ከዚሁ ጋር ተመሳሳይ የሆነውን አማርኛን ጨምሮ ባለብዙ ቋንቋ መጻፊያን simredo እዚህ ላይ [http://www.vc-net.ne.jp/~klivo/sim/simeng.htm simredo] ያገኙታል። ===<font size="+1">የሚሸጡ === ምሳሌ [http://www.geezedit.com Geezedit.com ግዕዝኤዲት.ኮም] ኣሉ። ይህን ዘዴ የሚያስረዳ ቪዲዮ [http://www.youtube.com/watch?v=YQZzwWuQS5Y እዚህ ይመልከቱ] በዩናይትድ አስቴትስ ፓተንት የተጠበቀ [[http://pdfpiw.uspto.gov/.piw?PageNum=0&docid=09000957&IDKey=176EEB253B91%0D%0A&HomeUrl=http%3A%2F%2Fpatft.uspto.gov%2Fnetacgi%2Fnph-Parser%3FSect1%3DPTO1%2526Sect2%3DHITOFF%2526d%3DPALL%2526p%3D1%2526u%3D%25252Fnetahtml%25252FPTO%25252Fsrchnum.htm%2526r%3D1%2526f%3DG%2526l%3D50%2526s1%3D9000957.PN.%2526OS%3DPN%2F9000957%2526RS%3DPN%2F9000957] ===<font size="+1">ፈጣን ዘዴ:-=== *<font size="+1">መላውን የግዕዝ ፊደሎች ለመፃፍ ለተቸገረ ወደ [http://www.branah.com/ethiopic www.branah.com] በመሔድ ከዚያም «ግዕዝ ሀበነ» የተባለውን ኪቦርድ በመምረጥ መፃፍ ይቻላል። ምንም አይነት ሶፍትዌር መጫን አያሰፈልግም። *<font size="+1">የአማርኛ መጻፊያ ሶፍትዌር ለመጫን ለተቸገረ ሰው ወደ [http://metatef.org መጣጥፍ]በመሄድ መጻፍ አንድ መፍትሄ ነው .ከዚያም copy/paste ወይም ገልብጦ መለጠፍ ይቻላል:: *<font size="+1">ወደ [http://www.cyberethiopia.com/warka4/index.php ዋርካ] ሂደው እዚያ ቀጥታ በፊደል ለመጻፍ ቀላል ነው። በማንኛውም ፎረም ውስጥ "አዲስ አርስት" በመጫን ነው። "Submit" ሳይጫኑ የ"መቀሱን" ምልክት ቢጫኑ የጻፉትን ወደ ኮምፒዩተርዎ "Clipboard" ያስቀምጠዋል። ከዚያ በሌላ መስኮት ውስጥ የጻፉትን ከክሊፕቦርድ ወደዚህ "paste" ማድረግ (Ctrl+v) ብቻ ነው! *<font size="+1">ሌላ ደግሞ [http://amharicdictionary.com "አምሃሪክ ዲክሸነሪ ዶት ኮም"] በተባለ ጠቃሚ ድረገጽ በቀጥታ በፊደል መጻፍ ይቻላል። *<font size="+1">በተጨማሪም [http://iyesus.com "ኢየሱስ ኮም"] በተባለ ድረገጽ በቀጥታ በፊደል መጻፍ ይቻላል። *<font size="+1">[https://typingkeyboards.com/amharic-keyboard/ የበአማርኛ ቁልፍ ሰሌዳ ይተይቡ።] ===<font size="+1">ፊደልና ኪይቦርድ የማይፈልግ አዲስ በፔንዲንግ ፓተንትና ፓተንት (pending patents) [http://pdfpiw.uspto.gov/.piw?PageNum=0&docid=09000957&IDKey=176EEB253B91%0D%0A&HomeUrl=http%3A%2F%2Fpatft.uspto.gov%2Fnetacgi%2Fnph-Parser%3FSect1%3DPTO1%2526Sect2%3DHITOFF%2526d%3DPALL%2526p%3D1%2526u%3D%25252Fnetahtml%25252FPTO%25252Fsrchnum.htm%2526r%3D1%2526f%3DG%2526l%3D50%2526s1%3D9000957.PN.%2526OS%3DPN%2F9000957%2526RS%3DPN%2F9000957] የተጠበቀ ዘዴ</font >=== *<font size="+1">[http://freetyping.geezedit.com ዓማርኛ ግዕዝኤዲት በነፃ GeezEdit Online እዚህ] ተጭነው ያገኙታል። [http://www.ethiopianamericanforum.com/index.php?view=article&id=486:dr-aberra-molla-interview-on-etv] የግዕዝ ቀለሞች በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ብቻ እንዲከተቡ የፈጠሩትን ኣዲስ ዘዴ ሕዝቡ በነፃ በኣማርኛ ዊንዶውስና ማክ ኮምፕዩተሮች ውስጥ እንዲጠቀምበት ኣበርክተዋል። የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግሩም ኣስተያየትም ኣለበት። [http://www.youtube.com/watch?v=CMQYuhaAKH4] ግዕዝኤዲት ቪዲዮ ፳፻፭ ዓ.ም.፣ 9/26/2012 የኣከታተብ እርዳታ በአማርኛ እዚህ [http://freetyping.geezedit.com/aTyping.htm] እና በእንግሊዝኛ እዚህ [http://freetyping.geezedit.com/Typing.htm] ኣሉ። *<font size="+1"> ምንም ሌላ ጥያቄ ካለዎ ወይም ችግር ቢያጋጥምዎ ማናቸውንም [[Special:Listusers/sysop|መጋቢ]] ይጠይቁ! birr steny [[bg:Уикипедия:Първи стъпки]] [[ky:Help:Contents]] 49y2cldpkjwem0uq324u6ihq0dsbfif ጦር መሳሪያ 0 11602 385932 385800 2025-06-26T17:31:50Z Eyu07 37572 ማስተካከያ 385932 wikitext text/x-wiki [[መደብ:ጠመንጃ]] [[ስዕል:AK-47 and SKS DD-ST-85-01268.jpg|thumb|470x470px|በምስሉ ላይ የሚታዩት ሁለቱ የጦር መሳሪያዎች የሶቭየት ህብረት የአሰራር ንድፍ ውጤቶች ናቸው። ከላይ የሚታየው ክላሽንኮቭ (AK-47) በአስተማማኝነቱና በቀላል አጠቃቀሙ በዓለም ዙሪያ ዝናን ሲያተርፍ፣ ከታች ያለው ኤስኬኤስ (SKS) ደግሞ ከፊል-አውቶማቲክ አቅሙና በትክክለኝነቱ ይታወቃል።]] '''ጦር መሳሪያ''' ለውጊያ የሚውል የመሳሪያ አይነት ሲሆን፣ በውስጡ ሚገባውን ጥይት በባሩድ ፈንጂ ኃይል ተጠቅሞ በከፍተኛ ፍጥነት በማስወንጨፍ ጉዳት ያደርሳል። የመጀመሪያዎቹ የጦር መሳሪያዎች በ10ኛው ክፍለ ዘመን ቻይና ውስጥ የተሰሩ ሲሆን፣ ጥቁር ባሩድን እንደ ፈንጅ ይጠቀሙ ነበር። ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች በአብዛኛው ጭስ አልባ ባሩድን ይጠቀማሉ እንዲሁም አብዛኛዎቹ (ከምንጃር ጠመንጃ(ሾት ጋን) በስተቀር) ስርስር አፈሙዝ አላቸው። ይህ ስርስር ጥይቱ በሚወነጨፍበት ጊዜ እንዲሽከረከር በማድረግ አቅጣጫውን ጠብቆ እንዲጓዝና ሩቅ ዒላማ በትክክል እንዲመታ ያስችለዋል። == የጦር መሳሪያዎች ምደባ == የጦር መሳሪያዎች በተለያዩ መስፈርቶች ይመደባሉ። ዋና ዋናዎቹ መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፦ === በመጠን እና በአጠቃቀም === ይህ ምደባ የጦር መሳሪያዎቹን አንድ ወታደር በቀላሉ ሊሸከማቸው ይችላል ወይ የሚለው ላይ ይመሰረታል። * '''ቀላል የጦር መሳሪያዎች፦''' አንድ እግረኛ ወታደር ብቻውን በቀላሉ ሊሸከማቸውና ሊጠቀምባቸው የሚችሉ ናቸው። እነዚህም "ትናንሽ የጦር መሳሪያዎች" በመባል ይታወቃሉ። * '''ከባድ የጦር መሳሪያዎች፦''' በመጠን በጣም ግዙፍና ከባድ በመሆናቸው አንድ ሰው ብቻውን ሊሸከማቸው አይችልም። በሚተኩሱበት ጊዜ የሚያስከትሉት እርግጫ ከፍተኛ ስለሆነ፣ ተንቀሳቃሽና ውጤታማ ለመሆን እንደ ተሽከርካሪ፣ ድጋፍ ወይም መደብ ይፈልጋሉ። === በማቀባበያ === ይህ ምደባ አንድ መሳሪያ ጥይቶችን እንዴት ወደ አፈሙዙ እንደሚያስገባና እንደሚተኩስ ላይ ያተኩራል። * '''አንድባንድ የሚሰራ(በተለምዶው ቁመህ ጠብቀኝ)፦''' ተጠቃሚው እያንዳንዱን ጥይት ከተኮሰ በኋላ ያገለገለውን ጥይት አስወጥቶ አዲስ ጥይት በእጅ ማስገባት አለበት። * '''ከፊል-አውቶማቲክ፦''' ቃታው ሲሳብ አንድ ጥይት ብቻ ይተኩሳል፣ ነገር ግን መሳሪያው በራሱ አዲስ ጥይት ያቀባብላል። ድጋሚ ለመተኮስ ቃታው ተለቆ ድጋሚ መሳብ አለበት። * '''ሙሉ-አውቶማቲክ፦''' ተጠቃሚው ቃታውን እስካለቀቀ ድረስ መሳሪያው ያለማቋረጥ እያቀባበለ እሩምታ መተኮሱን ይቀጥላል። == ዋና ዋና የጦር መሳሪያ ዓይነቶች == [[ስዕል:DesertEagle 50AE.jpg|thumb|356x356px|'''ዲዘርት ኢግል''' የእጅ ሽጉጥ : በዋናነት የሚታወቀው በመጠኑ ግዝፈትና እጅግ በጣም አደገኛ የሆኑ 50 '''ካሊበር''' ጥይቶችን የመተኮስ አቅሙ ነው።|left]] === የእጅ ሽጉጦች === በአንድ እጅ ለመያዝና ለመተኮስ የተሰሩ አጫጭር የጦር መሳሪያዎች ናቸው። * '''ፒስቶል፦''' ጥይቶቹ በመጋዘን (ካዝና) ውስጥ ተደርድረው የሚቀመጡ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ጥይት ከተተኮሰ በኋላ ቀጣዩ በራሱ ጊዜ ወደ መተኮሻው ቦታ ይገባል። * '''ሽክርክሪት ሽጉጥ (ሪቮልቨር)፦''' ጥይቶቹ በሚሽከረከር ከበሮ መሰል ክፍል ውስጥ ይቀመጣሉ። ቃታው ሲሳብ ከበሮው እየዞረ አዲስ ጥይት ወደ መተኮሻው ቦታ ያመጣል። === ረጅም የጦር መሳሪያዎች === [[ስዕል:SVD Dragunov.jpg|thumb|493x493px|ኤስቪዲ ድራጉኖቭ : የሶቭየት ህብረት ውጤት የሆነው ይህ ከፊል-አውቶማቲክ ጠመንጃ፣ የእግረኛ ጦርን የውጊያ ርቀት ለማስፋት የተሰራ የአነጣጥሮ ተኳሽ ጠመንጃ ነው። ]]በስደፍ ተደግፈው የሚተኮሱ እና ረጅም አፈሙዝ ያላቸው መሳሪያዎች ናቸው። * '''ጠመንጃ፦''' አፈሙዙ ውስጡ ስርስር ነው፤ ይህም ጥይቱ እየተሽከረከረ እንዲወጣ በማድረግ ርቀት ላይ ያለን ዒላማ በትክክል ለመምታት ያስችላል። * '''አልሞ ተኳሽ ጠመንጃ''' ''':-''' እነዚህ ጠመንጃዎች የተሰሩት ለረጅም ርቀት ተኩስ ከፍተኛ ትክክለኝነት እንዲኖራቸው ተደርገው ነው * '''የምንጃር ጠመንጃ:'''- ከሌሎች የጦር መሳሪያዎች የሚለየው ዋነኛ ባህሪው የአፈሙዙ ውስጣዊ ክፍል ልስልስ ያለ መሆኑ ነው።ይህ መሳሪያ የሚተኩሰው "የምንጃር ጥይት" ሲሆን፣ ይህ ጥይት በውስጡ በርካታ ትናንሽ የብረት ፍንጣሪዎችን (በአማርኛ '''ሽሮ''') በአንድ ላይ የያዘ ነው። እነዚህ "ሽሮዎች" ከአፈሙዙ ከወጡ በኋላ ስለሚበተኑ፣ በአጭር ርቀት ላይ ተንቀሳቃሽ ዒላማዎችን ለመምታት ከፍተኛ ውጤታማነት አላቸው። በእንግሊዝ አፍ ሾት ገን ይባላል። * '''ቅላል-መትረየስ፦''' አነስተኛ እና ቀላል ሆኖ ነገር ግን እንደ መትረየስ ፈጣን እሩምታ መተኮስ የሚችል መሳሪያ ነው። ከጠመንጃ የሚለየው የሚጠቀመው የሽጉጥ ጥይቶችን በመሆኑ ነው። * '''መትረየስ፦''' ለረጅም ጊዜ ያለማቋረጥ እሩምታ መተኮስ የሚችል፣ ሙሉ-አውቶማቲክ መሳሪያ ነው። ብዙውን ጊዜ የመደብ ድጋፍ ይፈልጋል። == ዓለም አቀፍ አምራቾች እና ስርጭት == === ታዋቂ አምራቾች === በዓለም ላይ ካሉ የጦር መሳሪያ አምራቾች መካከል ዋና ዋናዎቹ ብራውኒንግ፣ ሬሚንግተን፣ ኮልት፣ ሩገር፣ ስሚዝ ኤንድ ዌሰን (አሜሪካ)፤ ሄክለር እና ኮክ፣ ዋልተር (ጀርመን)፤ ግሎክ (ኦስትሪያ)፤ በሬታ (ጣሊያን)፤ ኖሪንኮ (ቻይና)፤ እንዲሁም ክላሽንኮቭ (ሩሲያ) ናቸው። === የጦር መሳሪያዎች ስርጭት === እ.ኤ.አ. በ2018 የወጣ አንድ ጥናት እንዳመለከተው፣ በዓለም ዙሪያ ከአንድ ቢሊዮን በላይ የጦር መሳሪያዎች ይገኛሉ። * '''857 ሚሊዮን''' (85%) የሚሆኑት በሰላማዊ ሰዎች እጅ ይገኛሉ። ከዚህ ውስጥ 393 ሚሊዮኑ የአሜሪካ ዜጎች እጅ ላይ ነው። * '''133 ሚሊዮን''' (13%) የሚሆኑት በጦር ኃይሎች ቁጥጥር ስር ናቸው። * '''23 ሚሊዮን''' (2%) የሚሆኑት በሕግ አስከባሪ ተቋማት እጅ ይገኛሉ። pfxjzbnia3zqpplhds5jthz8feyzq47 ንጉሥ ካሌብ ጻድቅ 0 52979 385934 378545 2025-06-27T06:15:31Z 196.188.245.35 385934 wikitext text/x-wiki {{infobox |abovestyle= background:#FFD300 |above= ንጉሥ ካሌብ |image=[[ስዕል:ዐፄ ካሌብ.jpeg|center|223px]] |caption=|headerstyle=background:#BCD4E6 |header1=[[:en:Kaleb of Axum|ጻድቅ ንጉሥ ዘኢትዮዽያ]] |headerstyle=background:#FFD300 |header16=<span style="color:#0048BA"> </span> |label2=የተወለደው |data2= በ፬፻ዎቹ አጋማሽ |label3=የነገሠበት ዘመን |data3=ከ፭፻፰ እስከ ፭፻፴፬ |label4=ቀዳሚ |data4=ንጉሥ ገብረመስቀል |label5=ተከታይ |data5=ንጉሥ አለሜዳ |label6=መንግሥት |data6=አክሱም |label7=የዘመኑ ገንዘብ መለዋወጫ |data7=[[ስዕል:Kaleb.jpg|160px|thumb|center|የአክሱማይት ካሌብ የመግዣ ገንዘቦች]] |label8=የንግሥ ቀን |data8=ግንቦት ፳ በኢትዮዽያ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን<br>ኦክቶበር 24 በካቶሊክ ቤተክርስቲያን |label9=የሚከበረው |data9=በ[http://www.ethiopianorthodox.org/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን]<br>በ[https://en.m.wikipedia.org/wiki/Eritrean_Orthodox_Tewahedo_Church በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን]<br>በ[https://en.m.wikipedia.org/wiki/Oriental_Orthodoxy ምሥራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን]<br>በ[[ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን]] |header10=}} ስመ ንግሡ ዳግማዊ ዐፄ እለ አጽብሐ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብሎ የተሰየመ ይህ የከበረ ጻድቅ የኢትዮጵያ ንጉሥ ካሌብ እግዚአብሔርን የሚፈራና በፍጹም ልቡ የሚወደው ሃይማኖቱም የቀና ሰው ነበረ ። ==ሥጋዊና መንፈሳወዊው ተጋድሎ ክፍል ፩== ከጌታችን [[እየሱስ ክርስቶስ|ከኢየሱስ ክርስቶስ]] ልደት አምስት መቶ ሃያ ዐራት ዓመት በኋላ በናግራን ሀገር በክርስቲያኖች በአይሁዶችና በአረማውያን መካከል ከባድ ፀብ ተነሣ<ref> [https://play.google.com/store/apps/details?id=com.sammy.mycountryquotes ታሪካቸው በኢትዮጵያ ሥንክሳር በግንቦት ፳ የሰማዕታትና ቅዱሳን ታሪክ ውስጥ ይነበባል]</ref> ። በዚህን ጊዜ ማዝሩቅ ወይም ፊንሐስ የተባለው የሂማሪያው ንጉሥ የአረመኔዎቹንና የአይሁዶቹን ምክር እየተቀበለ ክርስቲያኖቹን ፈጃቸው ። አብያተ ክርስቲያናቱንም ሁሉ አቃጠለ ። ከዚህ ሁሉ በፊት የከሓዲው ንጉሥ ክርስቲያኖቹን የናግራንን ሰዎች ፤ [[እየሱስ ክርስቶስ|ክርስቶስን]] ብትክዱት ሕይወታችሁ ይጠበቃል ። ማንኛውም መከራና ሥቃይ ወይም ጥፋት ሊያገኛችሁ አይችልም አለቸው ። እነዚህ ቅዱሳን ሰማዕታት ግን በአምላክነቱ አምነን በስሙ የተጠመቅን እኛስ ክርስቶስን ልንክደው አንችልም ሲሉ በታላቅ ቃል ጮሁ። ዳግመኛም ይህ አላዊ ንጉሥ አምላካችን የምትሉት ክርስቶስ ከእጄ የሚያድናችሁ ይመስላችኋልን? ከዚህ ከሚያስፈራና ከሚያስደነግጥ ሥቃይና መከራ ሊያወጣችሁ ይቻለዋልን? ወደዚህስ ቀርቦ ከእኔ ጋር ይዋጋ ዘንድ ይቻለዋልን አላቸው ። እኒህንም ቅዱሳን የዚህ አላዊ ንጉሥ አነጋገር አላስደነገጣቸውም ወይም አላስፈራቸውም ። ይልቁንም በመታበዩና በመታጀሩ ኅሊናቸው ስለተነካ በክርስቶስ እምነታችን የጸና ነው ። እርሱ ሁሉ በነፍስና በሥጋ ላይ ለመፍረድ ሥልጣን ያለውን ፍሩት እንጂ በሥጋችሁ ላይ የሞት ፍርድ የሚፈርዱትን አትፍሯቸው ሲል በቅዱስ ወንጌል ነግሮናልና ። ስለዚህ ስለ ክርስቶስ ስም መሞትን አንፈራም አሉት ። ከዚያም እሊህ ቅዱሳን ወንዱም ሴቱም ሽማግሌውም ወጣቱም በሙሉ ልባችን በክርስቶስ እምነት የጸና ነው ። ይህ ዓለም ያልፋል ይጠፋል ለኛ ግን ለዘለዓለም የማያረጅ የማይጠፋ ተስፋ ተሰጥቶናል ወይም ተዘጋጅቶልናል እያሉ በተባበረ ድምፅ ጩኸታቸውን አስተጋቡ። በዚያን ጊዜ የክርስቲያኖቹ መሪ በጣም ክቡር የሚሆንና የዘጠና አምስት ዓመት ዕድሜ ያለው ቅዱስ ሂሩት ከቤተሰቦቹ ጋር በከሃዲው ንጉሥ ፊት ለፍርድ ቀርቦ ሣለ ንጉሡ ፊንሐስ ፊቱን ወደሱ መለስ አድርጎ ሂሩት ሆይ ስማ ይህን ሁሉ መከራ ያመጣብህ በክርስቶስ በማመንህ ነውና እሱን አሁን ፈጥነህ ካደው አለው ። [[ሥላሴ|እግዚአብሔር]] የመረጠው ቅዱስ ኂሩትም አስቀድመው በመሐላ የገቡትን ቃል የማያከብሩና የተናገሩትን ቃል እንደማያስታውሱ እንዳንተ ያሉ ከሓዲዎች ፈጣሪዬን አልክድም ሲል በድፍረት መለሰለት። በዚህ ጊዜ ከሐዲው ንጉሥ በጣም ተቆጣና ቅዱስ ኂሩትን ወደሚገደልበት ቦታ ወስደው በሰይፍ እንዲገድሉት ጭፍሮቹን አዘዘ ። ክርስቲያኖቹም አባታቸው ወይም መሪያቸው ቅዱስ ሂሩት የከሐዲው ንጉሥ ጭፍሮች ወደሚገደልበት ሲወስዱት ባዩ ጊዜ አባታችን ቅዱስ ሂሩት ሆይ ከሞትህ የሙሽርነት ሠርግ አትለየን። እኛ በክርሰቶስ አምነን ከአንተ ጋር መሞት ይገባናልና አሉት። አባታቸው ቅዱስ ሂሩትም የእነዚህ ቅዱሳን ሰማዕት ቃላቸው ትክክል ነገራቸውም ዕውነት ፣ ቃል ኪዳናቸውም የጸና መሆኑን ፈጽሞ በተረዳ ጊዜ በእነዚህ ክርስቲያኖች ሕዝቦች ላይ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብሎ በትእምርተ መስቀል እያማተበ ባረካቸው። ከዚህም በኋላ ቅዱስ ኂሩት በንጉሡ ፍርድ ምንም ሳይፈራ በሃይማኖቱ እንደጸና ከቤተሰቦቹ ጋር አንገቱን በሰደፍ ተቆርጦ ሞትና የሰማዕትነት ክብር ተቀዳጀ ። በዚሁ ጊዜ ድማኅ የምትባል ሴት በንጉሡ ጭፍሮች ተይዛ ተገደለችና ከሱ ጋር በሰማዕትነት ዐረፈች ። እነዚህም ቅዱሳን ሰማዕታት እጃቸው የኋሊት ታሥሮ ሣለ እንደዚሁ በራሳቸው በትእምርተ መስቀል አምሣል አማተቡ። በዚያን ጊዜ ያ አረማዊ ንጉሥ ከሱ ጋር ያለ ፍርሐት በድፍረት በመነጋገራቸው በነዚህ ቅዱሳን ላይ እጅግ ተቆጣ ፤ ስለሃይማኖታቸው ጽናትና ስለልባቸውም ጭካኔ ልቡ በቅናት እንደ እሳት ነደደ ። ከንዴቱም የተነሣ ሰፊና ጥልቅ የሆነ ጉድጓድ ቆፍረው በውስጡ እሳት ያነዱ ዘንድ አዘዘ ፤ ከዚያም እሊህ ቅዱሳን ፈጣሪያቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው በጉድጓድ ውስጥ በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ ፈረደባቸውና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእሳት ተቃጥለው ሞቱ። እነዚህም ብዙዎቹ የናግራን ክርስቲያኖች በሚገደሉበት ጊዜ የረዳቶቻቸውን የቍስንጥንያንና [[ኢትዮጵያ|የኢትዮጵያን]] ነገሥታት ስም በጸሎታቸው እያነሱ በሰማዕትነት ሞቱ ። እኒህም በግፍ የተገደሉት ክርስቲያኖች ቍጥራቸው ሃያ ሺህ ነበር ። ዳግመኛም ይኸው አላዊና ጨካኝ ንጉሥ ፊንሐስ የኤጲስ ቆጶሱን የጳውሎስን አፅም ከመቃብር አስወጥቶ በእሳት አቃጠለው ። እንዲሁም ክርስቲያኖቹን ካሉበት እያደነ በእሳትና በሰይፍ አጠፋቸው። ከጥቂት ጊዜ በኋላ የቁስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳስ ጢሞቴዎስ በናግራን አገር ስለተፈጁት የክርስቲያን ወገኖች በግፍ የተጨፈጨፉበትን መላእክት የያዘች ደብዳቤ ወደ ኢትዮጵያው [[አክሱም]] ንጉሥ ወደ ዓፄ ካሌብ ላከ ። የኢትዮጵያው [[ንጉሠ ነገሥት|ንጉሠ ነገሥት]] ዓፄ ካሌብም ከወርቅ በተሠራው ዙፋኑ ላይ ትቀምጦ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በዙፋኑ ዙሪያ የጦር አለቆቹና መኳንንቶቹ በክብር አጅበውት ሳለ የሊቀ ጳጳሱ መልእክተኞች ወደ እርሱ ደርሰው የመልእክቱን ደብዳቤ አስረከቡ ። ንጉሠ ዓፄ ካሌብም የመልእክቱን ደብዳቤ ተቀብሎ ነገሩን ወይም ትርጉሙን ከተረዳ በኋላ መልእክተኞቹን ወደአገራቸው በሰላም አሰናበታቸው ። ከዚያም የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ዓፄ ካሌብ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ከፈቀደልኝስ በግፍ ስለተገደሉት ክርስቲያን ወገኖቼ የማደርገውን አውቃለሁ ሲል በልቡ አሰበ ። ==ተጋድሎ ክፍል ፪== ፪ ፤ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ዓፄ ካሌብ የናግራንን ሰዎች በግፍ መገደል ከሰማ በኋላ ወደ አባታችን ብፁዕና ቅዱስ የሚሆን ወደ [[አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ|አቡነ አረጋዊ]] እንዲህ ሲል ላከበት ። ይህ ፊንሐስ የተባለ አረማዊ የናግራንን ሰዎች ደም ያፈሰሰ ቤተ ክርስቲያንን የመዘበረና ያጠፋ ፍጹም የእግዚአብሔር ጠላት ወደሚሆን ሄጀ እዋጋው ዘንድ ተዘጋጅቻለሁ ። ሊቀ ጳጳሱ ጢሞቴዎስም የናግራንን ሰዎችና የሰማዕታቶቿንም ደም ተበቀል ሲል ወደኔ ልኮብኛልና ። ስለዚህ አባቴ ሆይ አንተም በበኩልህ ወደ ጌታዬና አምላኬ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸሎት አድርግልኝ ። የጻድቅ ጸሎት ትራባለች ፤ ኃይልንም ታሰጣለች፤ በጠላት ላይም ድልን ታቀዳጃለችና ሲል ላከበት ። አባታችን አቡነ አረጋዊም ለንጉሡ መልክተኛ እንዲህ አለው ። ንጉሡን ወደጦሩ ግንባር ሂድ ጠላቶችህን ከእግርህ በታች ያስገዛልህ ተፋላሚዎችህንም እግዚአብሔር በጭፍሮችህ እጅ ይጣላቸው። ለአንተም ታላቅ ግርማ ሞገስ ይስጥህ ። በሰላም ይመልስህ ብለህ ንገረው አለውና እርሱም ይህንኑ ነገረው ። የኢትዮጵያው ንጉሥ ዓፄ ካሌብም ለጦርነት ጉዞውን ከመቀጠሉ በፊት ወደቤተ ከርስቲያን ሄዶ ልብሰ መንግሥቱን አውልቆ ፣ ማቅ ለብሰ። አቅርንተ ምሥዋውን እየተማፀነ ዓይኑን ወደ ሰማይ አቅንቶ እንዲህ እያለ ጸለየ ። አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ በሰማይም በምድርም ያለውን ሁሉ የፈጠርክ እልፍ አእላፍ መላእክት የሚገዙልህ ኪሩቤልና ሱራፌል የሚያመሰግኑህ የካህናት ፈጣሪያቸው ። አቤቱ የጌቶች ጌታ የነገሥታትም ንጉሥ የምትሆን የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባት ብርሃናትን የፈጠርክ ሰውን ሁሉ ከኃሣር ወደ ዘለዓለም ክብር ይመልስ ዘንድ አንድ ልጅህን ወደኛ የላክኸው ። አቤቱ የአባቶቻችን ፈጣሪያቸውና አምላካቸው ሆይ እኛን ስለማዳን ፍጹም ሰው በሆነው ልጅህ ምክንያት ይህ ከሐዲ ፊንሐስ ያደረገውን እነሆ አይተኸዋል። ወገኖችህንም እንደ በግ እንዳረዳቸውና አብያተ ክርስቲያናትህንም እንዳቃጠለ ተመልክተነዋል። አቤቱ እነሆ ከዚህ ወጥቼ ይህን ያንተንና የኛንም ጠላት ከሐዲ አይሁዳዊ በአንድ ልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል አጠፋዋለሁ ። ስለሆነም አቤቱ አታሳፍረኝ ስለ አንተ ስለፈጣሪዬና ስለ ክርስቲያን ወንድሞቼ ቅናት አድሮብኛልና ። አቤቱ ቦኃጢአቴ ብዛት ጸሎቴን የማትቀበል ልመናዬን የማትሰማ ከሆነ ግን በዚች በቆምኩባት ቦታ በአሁኑ ሰዓት ሕይወቴ ታልፍ ዘንድ ፈቃድህ ይሁን ። አቤቱ ጌታዬና አምላኬ ሆይ ፤ ርስትህ የምትሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ ስምህን በማያውቁ ጠላቶችህ እጅ አሳልፈህ አትስጣቸው ሲል አጥብቆ ለመነ ። ኢትዮጵያዊው ንጉሥ ካሌብም ታላቅ ጻድቅ ሰው ነበር ከምድር ነገሥታት ወገን በመንግሥቱ ዙፋን ላይ ተቀምጦ እያለ ማንም እንደሱ ድንቅ ተአምራት ያደረገ የለም ። ከሁሉም በፊት የዑር አገር ሰዎች ባመፁበት ጊዜ የሀገሪቱ ሰዎች የጦሩን መትመምና ግስጋሤ አይተው እንዳይሸሹና እንዳያመልጡ እግዚአብሔር በምድር ውስጥ መንገድ ከፈተለት ። የመንገዱም ርዝመት መጠን ለጐበዝ ተራማጅ ወይም ፈጣን ሩዋጭ ሰው ሦስት ቀን የሚያስኬድ ጐዳና ነበር ። ከዚያም እግዚአብሔር በመሬት ውስጥ በከፈተለት መንገድ ገብቶ ገሥግሶ ድንገት ደረሰና ደመሰሳቸው አጠፋቸውም ። ከነሱ አንድ ስንኳ አላስቀረም ። ሀገሪቱንም በእጁ አገባት እስከ ዛሬም ድረስ አለች ። ==ተጋድሎ ክፍል፫== ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ይኸው የኢትዮጵያ ንጉሥ እፄ ካሌብ ሰባ ሺህ የሚደርሰውን ጦሩን አስከትቶና አዘጋጅቶ ቀድሞ ወደ አሰበበት ወደ የመን በመርከብ ተጓዘ ። ከዚያም የኢትዮጵያው ንጉሥ ካሌብ ከመርከብ ሲወርድ ጠብቆ ከሐዲው ንጉሥ ብዙ ጦር አሰልፎ ካሌብን ወጋው ። በመካከላቸውም የሚደረገው ጦርነት በጣም የበረታ ሆነ ። ያን ጊዜም ካሌብና የጦር ሠራዊቱ በጦርነቱ መካከልና በጠላቶቻቸው ፊት እጅግ በረቱ ። የከሐዲውን ንጉሥ ሠራዊትም አሸንፈው በታተኗቸው ። ይልቁንም ካሌብ እራሱ ያን ከሐዲ ንጉሥ ፊንሐስን ገጠመውና በፈረሱ ላይ እንደ ተቀመጠ በጨበጣ በጦር ወግቶ ገደለውና ወደ ባሕር ገልብጦ ጣለለው። ያም ከሐዲው ንጉሥ ከዚያው ሰጥሞ ሞተ ፤ ሚስቱም በዚሁ ጊዜ ተማረከች ። ከዚያም በኋላ አፄ ካሌብ ዛፋር ፣ ወደምትባለው ወደ ሳባ ከተማ በታላቅ ግርማ ገስግሦ ሄደ ። የከተማውንም ጠባቂዎች አሸንፎ ገብቶ፣ ከተማዋን ያዘ ። ይህም የተደረገው ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በኋላ በአምስት መቶ ሃያ አምስት ዓመተ ምሕረት ላይ ነው ። ፲፬ ፣ ከዚህም በኋላ በዛፋር ከተማ ውስጥ እየተዘዋወረ በክርስቲያኖቹ እልቂት ዕለት ደም በማፍሰስ የተባበሩትን የከሐዲውን የፊንሐስን ሹማምንት እያስፈለገ አስያዘና በአደባባይ በማስገደል በሀገረ ናግራን የተፈጁትን ክርስቲያኖች ደማቸውን በሚገባ ተበቀለ ። የተረፉት ክርስቲያኖችም ከሸሹበትና ከተሸሸጉበት ወደ ቀደመ ቦታቸው ተመለሱ ። ኢትዮጵያዊው ንጉሥ አፄ ካሌብም የድል አድራጊነትን አክሊል እንደ ተቀዳጀ ለእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ መልእክት ላከ ። ሊቀ ጳጳሱም ወደ ቍስጥንጥንያው ንጉሥ ይህንኑ የደስታ መልእክት አስተላለፈና በሁሉም ዘንድ ታላቅ ደስታ ተደረገ በዚያን ጊዜ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አንድ ኤጲስ ቆጶስ ሾሞ ወደ ብሔረ ሳባ ላከ። ኢትዮጵያዊው ንጉሥ አፄ ካሌብም የአይሁዱ ንጉሥ በሚገዛበት በዚያ ግዛት ሁሉ ቤተ ክርስቲያን አሣነፀ ። ለቤተ ክርስቲያኑም መሠረት እራሱ ዓፄ ካሌብ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ሲያስቆፍር ሰነበተ ። ከዚያም ታላቅ በዓል አድርጐ እግዚአብሔርን አመሰገነው ። ያ የክርስቶስ ጠላት አረማዊ ንጉሥ የመዘበራትንና ያጠፋትን ቤተ ክርስቲያን በናግራን ሀገር ላይ እንደገና አሣነፀ ። ከሳባ ሀገር የማረከውን ንብረት ገንብና ጌጣ ጌጥ ሁሉ ለቤተ ከርስቲያኗ ክብር ሰጠ ። ከዚያም ለዚያች ለብሔረ ሳባ ስሙ አብርሃ የሚባል ብልህና ዐዋቂ ሰው መርጦ ሾመላቸው ። ቀጥሎም ገዥውን አብርሃንና ኤጲስ ቆጶሱን የሚጠብቁ ዓሥር ሺህ የጦር ሠራዊት መደበላቸው ። ከዚህ በኋላ ወደ ሀገሩ ወደ አክሱም በፍጹም ደስታና ፍሥሐ በድል አድራጊነት በሰላም ተመልሶ ገባ ። የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ የክርስቲያን አምላካቸው እግዚአብሔር በዚህ ኃያልና ተጋዳይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ በዓፄ ካሌብ እጅ ያደረገውን ድንቅ ሥራ ተመልከቱ። ይህ ዓፄ ካሌብ የአክሱምን መንግሥት የጥንት ግዛቱን በድል አድራጊነት በማስመላሱ የታወቀ አስፈሪና ገናና ንጉሥ ሆኗልና ። ይልቁንም በናግራን የተፈጁትን ክርስቲያኖች ደም በመበቀሉ በእስክንድርያ በቍስጥንጥንያ በአንጾኪያና በሮም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ ኀዘናቸው ወደ ደስታ እንዲለወጥ አድርጓልና። ይህ አማናዊ ንጉሥ ከዓረብ ሀገር ፈጽሞ ሊጠፋ የነበረውን የክርስትና አምልኮ ወደ ጥንት ቦታው መልሶ አቃናው። በቃል ኪዳን ጓደኝነት አንድ ሆነው በነበሩት በአይሁድና በፋርስ ሕዝብ ላይ አደጋ ጥሎ ከዐረብ አገር ግዛታቸውን አስወግዶ ክብራቸውን አሳንሶ እነሱንም አባሮ የራሱን አስተዳደር ተክቶና ገናንነቱን አሳውቆ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት አደላደለ ። ስለዚህ ይህ ታላቅ የኢትዮጵያ [[ንጉሠ ነገሥት]] ዓፄ ካሌብ በምሥራቅ በቍስጥንጥንያና በአረቦችም በቤተ መንግሥቱም በቤተ ክህነቱም በሁሉም ዘንድ ታላቅ ስመ ጥርና ሰፊ ታሪክ ያለው ሆነ ። ክብሩም ከተጋዳዮች ቅዱሳንና ከታላላቅ ሰማዕታት ክብር ጋር የተካከለ ሆነ ። ስለዚህም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመታሰቢያውን በዓል በጥልቅ ስሜት ታከብራለች ። የምታከብረውም የኛ ቤተ ክርስቲያን ብቻ አይደለችም ። ነገር ግን የሮማም ቤተ ክርስቲያን የመታሰቢያውን በዓል ከሌሎቹ አሸናፊዎች ሰማዕታት በዓል ጋር በማስተካከል በጥቅምት ሃያ ሰባት ቀን በታላቅ ክብርና በብዙ ደስታ ታከብረዋለች እንጂ ==መንፈሳዊ ብቃት== የኢትዮጵያው ንጉሥ አፄ ካሌብ በናግራን ሀገር ጦርነት ድልን ተቀዳጅቶ ከተመስሰ በኋላ ኃይልና መጠጊያ ረዳቴና አዳኜ የሚሆን እግዚእብሔርን ምን አድርጌ ላስደስተው ሲል አሰበና የዚህን ዓለም መንግሥት ተድላ ደስታ ንቆ ልብሰ መንግሥቱን አውልቆ አንዲት የውሃ መንቀልና አንዲት ምንጣፍ ብቻ ይዞ አባ ጰንጠሌዎን ገዳም አጠገብ ከሚገኝ ዋሻ ወስጥ ገብቶ በአባ ጰንጠሌዎን እጅ መንኩሶ ለመቀመጥ ወሰነ ። አባ ጰንጠሌዎንንም አመንኵሰኝ አለውና የመላእክትን አስኬማ አልብሶ አመነኰሰው ። ዳግመኛም ከዋሻ ወይም ከገዳም ወጥቶ ዓለምን በዓይኑ ላለማየት ማለ ቃል ኪዳንም ገባ። ቤተ መንግሥቱን ለቆ ወደ ምናኔ በሄደበት ጊዜ ዋጋው እጅግ የከበረውንና በነገሠ ጊዜ የጫነውን የወርቅ ዘውዱን ከጌታችን አንቀጸ መቃብር ላይ ይሰቅልለት ዘንድ ከአደራ ደብዳቤ ጋራ ለኢየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳስ ለአባ ዮሐንስ ላከለት። ዳግመኛም ንጉሥ ዓፄ ካሌብ አባቴ ሆይ በአንተ ጸሎት በእግዚአብሔር ቸርነት ከጦርነቱ በሰላም ተመልሻለሁ አሁንም የክርስቶስን አርዑተ መስቀል ተሽክሜአለሁና እግዚአብሔር ለፍጻሜው ያብቃህ እያልክ ስለኔ ጸልይልኝ ሲል ወደ አባታችን ወደ አቡነ አረጋዊ ላከበት ። ስለዚህም ነገር አባታችን አቡነ አረጋዊ በጣም ተደስቶ ልጄ ሆይ መልካሙን የበለጠውን አድርገሃል። አሁንም እግዚአብሔር የፈቀድከውን ነገር ሁሉ ይፈጽምልህ በለው አለው። መልክተኛውም ይህን ከሰማ በኋላ ከአባታችን ከአቡነ አረጋዊ ዘንድ በረከትን ተቀብሎ ወደ መጣበት ተመልሶ ሄደ። ኢትዮጵያዊው ንጉሥ ዓጼ ካሌብ ይህን ዓለም በመናቅ በበረኃ በዋሻ ዐሥራ ሁለት ዓመት በጾምና በጸሎት በብዙ ተጋድሎ ሲኖር በግንቦት ሃያ ቀን ዐርፎ እስከ ዘለዓስሙ ድረስ የማያልፍ [[ሰማያዊ]] ክብርን ወረሰ ። የተወደዳችሁ ወንድሞች ጻድቅና ትሑት የሚሆን የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዓፄ ካሌብ በፈጣሪው በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ያደረገውን ድንቅ ሥራ እስኪ ተመልከቱ ። የሱና የፈጣሪውን ጠላቶች ዓላውያን ነገሥታት ባጠፋና የጦር ኃይላቸውን በደመሰሰ ጊዜ በኃይሉ አልተመካምና። ከጦር ሜዳም በድል አድራጊነት በተመለሰ ጊዜ ጐልያድን እንደ ገደለ እንደ ዳዊት ዘፋኞች ይዘፍኑለት ወይም ያሞግሱት ዘንድ አልወደደም። ነገር ግን የዚህን ዓለም መንግሥት ንቆ ወደ ምድረ በዳ ወይም በረሃ ገብቶ በትንሽ ዋሻ ውስጥ መኖርን ወደደ እንጂ ። ሎጥ ከሰዶምና ከገሞራ በሚወጣበት ጊዜ መላእክት እስኪያቻኩሉት ድረስ ወዲያ ወዲህ በማለት ለመዘግየት አልፈለገም ። የጨው ዓምድ እንደሆነችው እንደ ሎጥ ሚስትም ክብሩን በማሰብ ፊቱን ወደ ኋላው አልመለሰም ። እንግዲሀ ከኢትዮጵያዊው ንጉሠ ነገሥት ከካሌብ በስተቀር በሚታየው ክብር የማይታየውን ክብር ለውጦ በቆራጥነት ይህን ዓለም ንቆ ሁለተኛ ላለመመለስ ወደፊት ገሥግሶ በረኃ የገባ ማነው እሱ? እኛም እግረ ኅሊናችንን በቀና ጐዳና ይመራልን ዘንድ እግዚአብሔርን እንለም ነው ። ርስተ ወመንግሥተ ሰማያትንም ለመውረስ ዕድል ፈንታችንን ከቅዱሳኖቹጋር ያድርግልን ለዘለዓለሙ አሜን ። mpc51o6m4rhfxnt4imc6i8opsejti3d 385935 385934 2025-06-27T06:15:59Z 196.188.245.35 385935 wikitext text/x-wiki {{infobox |abovestyle= background:#FFD300 |above= ንጉሥ ካሌብ |image=[[ስዕል:ዐፄ ካሌብ.jpeg|center|223px]] |caption=|headerstyle=background:#BCD4E6 |header1=[[:en:Kaleb of Axum|ጻድቅ ንጉሥ ዘኢትዮዽያ]] |headerstyle=background:#FFD300 |header16=<span style="color:#0048BA"> </span> |label2=የተወለደው |data2= በ፬፻ዎቹ አጋማሽ |label3=የነገሠበት ዘመን |data3=ከ፭፻፰ እስከ ፭፻፴፬ |label4=ቀዳሚ |data4=ንጉሥ ገብረመስቀል |label5=ተከታይ |data5=ንጉሥ አለሜዳ |label6=መንግሥት |data6=አክሱም |label7=የዘመኑ ገንዘብ መለዋወጫ |data7=[[ስዕል:Kaleb.jpg|160px|thumb|center|የአክሱማይት ካሌብ የመግዣ ገንዘቦች]] |label8=የንግሥ ቀን |data8=ግንቦት ፳ በኢትዮዽያ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን<br>ኦክቶበር 24 በካቶሊክ ቤተክርስቲያን |label9=የሚከበረው |data9=በ[http://www.ethiopianorthodox.org/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን]<br>በ[https://en.m.wikipedia.org/wiki/Eritrean_Orthodox_Tewahedo_Church በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን]<br>በ[https://en.m.wikipedia.org/wiki/Oriental_Orthodoxy ምሥራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን]<br>በ[[ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን]] |header10=}} ስመ ንግሡ ዳግማዊ ዐፄ እለ አጽብሐ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብሎ የተሠየመ ። ይህ የከበረ ጻድቅ የኢትዮጵያ ንጉሥ ካሌብ እግዚአብሔርን የሚፈራና በፍጹም ልቡ የሚወደው ሃይማኖቱም የቀና ሰው ነበረ ። ==ሥጋዊና መንፈሳወዊው ተጋድሎ ክፍል ፩== ከጌታችን [[እየሱስ ክርስቶስ|ከኢየሱስ ክርስቶስ]] ልደት አምስት መቶ ሃያ ዐራት ዓመት በኋላ በናግራን ሀገር በክርስቲያኖች በአይሁዶችና በአረማውያን መካከል ከባድ ፀብ ተነሣ<ref> [https://play.google.com/store/apps/details?id=com.sammy.mycountryquotes ታሪካቸው በኢትዮጵያ ሥንክሳር በግንቦት ፳ የሰማዕታትና ቅዱሳን ታሪክ ውስጥ ይነበባል]</ref> ። በዚህን ጊዜ ማዝሩቅ ወይም ፊንሐስ የተባለው የሂማሪያው ንጉሥ የአረመኔዎቹንና የአይሁዶቹን ምክር እየተቀበለ ክርስቲያኖቹን ፈጃቸው ። አብያተ ክርስቲያናቱንም ሁሉ አቃጠለ ። ከዚህ ሁሉ በፊት የከሓዲው ንጉሥ ክርስቲያኖቹን የናግራንን ሰዎች ፤ [[እየሱስ ክርስቶስ|ክርስቶስን]] ብትክዱት ሕይወታችሁ ይጠበቃል ። ማንኛውም መከራና ሥቃይ ወይም ጥፋት ሊያገኛችሁ አይችልም አለቸው ። እነዚህ ቅዱሳን ሰማዕታት ግን በአምላክነቱ አምነን በስሙ የተጠመቅን እኛስ ክርስቶስን ልንክደው አንችልም ሲሉ በታላቅ ቃል ጮሁ። ዳግመኛም ይህ አላዊ ንጉሥ አምላካችን የምትሉት ክርስቶስ ከእጄ የሚያድናችሁ ይመስላችኋልን? ከዚህ ከሚያስፈራና ከሚያስደነግጥ ሥቃይና መከራ ሊያወጣችሁ ይቻለዋልን? ወደዚህስ ቀርቦ ከእኔ ጋር ይዋጋ ዘንድ ይቻለዋልን አላቸው ። እኒህንም ቅዱሳን የዚህ አላዊ ንጉሥ አነጋገር አላስደነገጣቸውም ወይም አላስፈራቸውም ። ይልቁንም በመታበዩና በመታጀሩ ኅሊናቸው ስለተነካ በክርስቶስ እምነታችን የጸና ነው ። እርሱ ሁሉ በነፍስና በሥጋ ላይ ለመፍረድ ሥልጣን ያለውን ፍሩት እንጂ በሥጋችሁ ላይ የሞት ፍርድ የሚፈርዱትን አትፍሯቸው ሲል በቅዱስ ወንጌል ነግሮናልና ። ስለዚህ ስለ ክርስቶስ ስም መሞትን አንፈራም አሉት ። ከዚያም እሊህ ቅዱሳን ወንዱም ሴቱም ሽማግሌውም ወጣቱም በሙሉ ልባችን በክርስቶስ እምነት የጸና ነው ። ይህ ዓለም ያልፋል ይጠፋል ለኛ ግን ለዘለዓለም የማያረጅ የማይጠፋ ተስፋ ተሰጥቶናል ወይም ተዘጋጅቶልናል እያሉ በተባበረ ድምፅ ጩኸታቸውን አስተጋቡ። በዚያን ጊዜ የክርስቲያኖቹ መሪ በጣም ክቡር የሚሆንና የዘጠና አምስት ዓመት ዕድሜ ያለው ቅዱስ ሂሩት ከቤተሰቦቹ ጋር በከሃዲው ንጉሥ ፊት ለፍርድ ቀርቦ ሣለ ንጉሡ ፊንሐስ ፊቱን ወደሱ መለስ አድርጎ ሂሩት ሆይ ስማ ይህን ሁሉ መከራ ያመጣብህ በክርስቶስ በማመንህ ነውና እሱን አሁን ፈጥነህ ካደው አለው ። [[ሥላሴ|እግዚአብሔር]] የመረጠው ቅዱስ ኂሩትም አስቀድመው በመሐላ የገቡትን ቃል የማያከብሩና የተናገሩትን ቃል እንደማያስታውሱ እንዳንተ ያሉ ከሓዲዎች ፈጣሪዬን አልክድም ሲል በድፍረት መለሰለት። በዚህ ጊዜ ከሐዲው ንጉሥ በጣም ተቆጣና ቅዱስ ኂሩትን ወደሚገደልበት ቦታ ወስደው በሰይፍ እንዲገድሉት ጭፍሮቹን አዘዘ ። ክርስቲያኖቹም አባታቸው ወይም መሪያቸው ቅዱስ ሂሩት የከሐዲው ንጉሥ ጭፍሮች ወደሚገደልበት ሲወስዱት ባዩ ጊዜ አባታችን ቅዱስ ሂሩት ሆይ ከሞትህ የሙሽርነት ሠርግ አትለየን። እኛ በክርሰቶስ አምነን ከአንተ ጋር መሞት ይገባናልና አሉት። አባታቸው ቅዱስ ሂሩትም የእነዚህ ቅዱሳን ሰማዕት ቃላቸው ትክክል ነገራቸውም ዕውነት ፣ ቃል ኪዳናቸውም የጸና መሆኑን ፈጽሞ በተረዳ ጊዜ በእነዚህ ክርስቲያኖች ሕዝቦች ላይ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብሎ በትእምርተ መስቀል እያማተበ ባረካቸው። ከዚህም በኋላ ቅዱስ ኂሩት በንጉሡ ፍርድ ምንም ሳይፈራ በሃይማኖቱ እንደጸና ከቤተሰቦቹ ጋር አንገቱን በሰደፍ ተቆርጦ ሞትና የሰማዕትነት ክብር ተቀዳጀ ። በዚሁ ጊዜ ድማኅ የምትባል ሴት በንጉሡ ጭፍሮች ተይዛ ተገደለችና ከሱ ጋር በሰማዕትነት ዐረፈች ። እነዚህም ቅዱሳን ሰማዕታት እጃቸው የኋሊት ታሥሮ ሣለ እንደዚሁ በራሳቸው በትእምርተ መስቀል አምሣል አማተቡ። በዚያን ጊዜ ያ አረማዊ ንጉሥ ከሱ ጋር ያለ ፍርሐት በድፍረት በመነጋገራቸው በነዚህ ቅዱሳን ላይ እጅግ ተቆጣ ፤ ስለሃይማኖታቸው ጽናትና ስለልባቸውም ጭካኔ ልቡ በቅናት እንደ እሳት ነደደ ። ከንዴቱም የተነሣ ሰፊና ጥልቅ የሆነ ጉድጓድ ቆፍረው በውስጡ እሳት ያነዱ ዘንድ አዘዘ ፤ ከዚያም እሊህ ቅዱሳን ፈጣሪያቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው በጉድጓድ ውስጥ በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ ፈረደባቸውና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእሳት ተቃጥለው ሞቱ። እነዚህም ብዙዎቹ የናግራን ክርስቲያኖች በሚገደሉበት ጊዜ የረዳቶቻቸውን የቍስንጥንያንና [[ኢትዮጵያ|የኢትዮጵያን]] ነገሥታት ስም በጸሎታቸው እያነሱ በሰማዕትነት ሞቱ ። እኒህም በግፍ የተገደሉት ክርስቲያኖች ቍጥራቸው ሃያ ሺህ ነበር ። ዳግመኛም ይኸው አላዊና ጨካኝ ንጉሥ ፊንሐስ የኤጲስ ቆጶሱን የጳውሎስን አፅም ከመቃብር አስወጥቶ በእሳት አቃጠለው ። እንዲሁም ክርስቲያኖቹን ካሉበት እያደነ በእሳትና በሰይፍ አጠፋቸው። ከጥቂት ጊዜ በኋላ የቁስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳስ ጢሞቴዎስ በናግራን አገር ስለተፈጁት የክርስቲያን ወገኖች በግፍ የተጨፈጨፉበትን መላእክት የያዘች ደብዳቤ ወደ ኢትዮጵያው [[አክሱም]] ንጉሥ ወደ ዓፄ ካሌብ ላከ ። የኢትዮጵያው [[ንጉሠ ነገሥት|ንጉሠ ነገሥት]] ዓፄ ካሌብም ከወርቅ በተሠራው ዙፋኑ ላይ ትቀምጦ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በዙፋኑ ዙሪያ የጦር አለቆቹና መኳንንቶቹ በክብር አጅበውት ሳለ የሊቀ ጳጳሱ መልእክተኞች ወደ እርሱ ደርሰው የመልእክቱን ደብዳቤ አስረከቡ ። ንጉሠ ዓፄ ካሌብም የመልእክቱን ደብዳቤ ተቀብሎ ነገሩን ወይም ትርጉሙን ከተረዳ በኋላ መልእክተኞቹን ወደአገራቸው በሰላም አሰናበታቸው ። ከዚያም የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ዓፄ ካሌብ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ከፈቀደልኝስ በግፍ ስለተገደሉት ክርስቲያን ወገኖቼ የማደርገውን አውቃለሁ ሲል በልቡ አሰበ ። ==ተጋድሎ ክፍል ፪== ፪ ፤ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ዓፄ ካሌብ የናግራንን ሰዎች በግፍ መገደል ከሰማ በኋላ ወደ አባታችን ብፁዕና ቅዱስ የሚሆን ወደ [[አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ|አቡነ አረጋዊ]] እንዲህ ሲል ላከበት ። ይህ ፊንሐስ የተባለ አረማዊ የናግራንን ሰዎች ደም ያፈሰሰ ቤተ ክርስቲያንን የመዘበረና ያጠፋ ፍጹም የእግዚአብሔር ጠላት ወደሚሆን ሄጀ እዋጋው ዘንድ ተዘጋጅቻለሁ ። ሊቀ ጳጳሱ ጢሞቴዎስም የናግራንን ሰዎችና የሰማዕታቶቿንም ደም ተበቀል ሲል ወደኔ ልኮብኛልና ። ስለዚህ አባቴ ሆይ አንተም በበኩልህ ወደ ጌታዬና አምላኬ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸሎት አድርግልኝ ። የጻድቅ ጸሎት ትራባለች ፤ ኃይልንም ታሰጣለች፤ በጠላት ላይም ድልን ታቀዳጃለችና ሲል ላከበት ። አባታችን አቡነ አረጋዊም ለንጉሡ መልክተኛ እንዲህ አለው ። ንጉሡን ወደጦሩ ግንባር ሂድ ጠላቶችህን ከእግርህ በታች ያስገዛልህ ተፋላሚዎችህንም እግዚአብሔር በጭፍሮችህ እጅ ይጣላቸው። ለአንተም ታላቅ ግርማ ሞገስ ይስጥህ ። በሰላም ይመልስህ ብለህ ንገረው አለውና እርሱም ይህንኑ ነገረው ። የኢትዮጵያው ንጉሥ ዓፄ ካሌብም ለጦርነት ጉዞውን ከመቀጠሉ በፊት ወደቤተ ከርስቲያን ሄዶ ልብሰ መንግሥቱን አውልቆ ፣ ማቅ ለብሰ። አቅርንተ ምሥዋውን እየተማፀነ ዓይኑን ወደ ሰማይ አቅንቶ እንዲህ እያለ ጸለየ ። አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ በሰማይም በምድርም ያለውን ሁሉ የፈጠርክ እልፍ አእላፍ መላእክት የሚገዙልህ ኪሩቤልና ሱራፌል የሚያመሰግኑህ የካህናት ፈጣሪያቸው ። አቤቱ የጌቶች ጌታ የነገሥታትም ንጉሥ የምትሆን የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባት ብርሃናትን የፈጠርክ ሰውን ሁሉ ከኃሣር ወደ ዘለዓለም ክብር ይመልስ ዘንድ አንድ ልጅህን ወደኛ የላክኸው ። አቤቱ የአባቶቻችን ፈጣሪያቸውና አምላካቸው ሆይ እኛን ስለማዳን ፍጹም ሰው በሆነው ልጅህ ምክንያት ይህ ከሐዲ ፊንሐስ ያደረገውን እነሆ አይተኸዋል። ወገኖችህንም እንደ በግ እንዳረዳቸውና አብያተ ክርስቲያናትህንም እንዳቃጠለ ተመልክተነዋል። አቤቱ እነሆ ከዚህ ወጥቼ ይህን ያንተንና የኛንም ጠላት ከሐዲ አይሁዳዊ በአንድ ልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል አጠፋዋለሁ ። ስለሆነም አቤቱ አታሳፍረኝ ስለ አንተ ስለፈጣሪዬና ስለ ክርስቲያን ወንድሞቼ ቅናት አድሮብኛልና ። አቤቱ ቦኃጢአቴ ብዛት ጸሎቴን የማትቀበል ልመናዬን የማትሰማ ከሆነ ግን በዚች በቆምኩባት ቦታ በአሁኑ ሰዓት ሕይወቴ ታልፍ ዘንድ ፈቃድህ ይሁን ። አቤቱ ጌታዬና አምላኬ ሆይ ፤ ርስትህ የምትሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ ስምህን በማያውቁ ጠላቶችህ እጅ አሳልፈህ አትስጣቸው ሲል አጥብቆ ለመነ ። ኢትዮጵያዊው ንጉሥ ካሌብም ታላቅ ጻድቅ ሰው ነበር ከምድር ነገሥታት ወገን በመንግሥቱ ዙፋን ላይ ተቀምጦ እያለ ማንም እንደሱ ድንቅ ተአምራት ያደረገ የለም ። ከሁሉም በፊት የዑር አገር ሰዎች ባመፁበት ጊዜ የሀገሪቱ ሰዎች የጦሩን መትመምና ግስጋሤ አይተው እንዳይሸሹና እንዳያመልጡ እግዚአብሔር በምድር ውስጥ መንገድ ከፈተለት ። የመንገዱም ርዝመት መጠን ለጐበዝ ተራማጅ ወይም ፈጣን ሩዋጭ ሰው ሦስት ቀን የሚያስኬድ ጐዳና ነበር ። ከዚያም እግዚአብሔር በመሬት ውስጥ በከፈተለት መንገድ ገብቶ ገሥግሶ ድንገት ደረሰና ደመሰሳቸው አጠፋቸውም ። ከነሱ አንድ ስንኳ አላስቀረም ። ሀገሪቱንም በእጁ አገባት እስከ ዛሬም ድረስ አለች ። ==ተጋድሎ ክፍል፫== ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ይኸው የኢትዮጵያ ንጉሥ እፄ ካሌብ ሰባ ሺህ የሚደርሰውን ጦሩን አስከትቶና አዘጋጅቶ ቀድሞ ወደ አሰበበት ወደ የመን በመርከብ ተጓዘ ። ከዚያም የኢትዮጵያው ንጉሥ ካሌብ ከመርከብ ሲወርድ ጠብቆ ከሐዲው ንጉሥ ብዙ ጦር አሰልፎ ካሌብን ወጋው ። በመካከላቸውም የሚደረገው ጦርነት በጣም የበረታ ሆነ ። ያን ጊዜም ካሌብና የጦር ሠራዊቱ በጦርነቱ መካከልና በጠላቶቻቸው ፊት እጅግ በረቱ ። የከሐዲውን ንጉሥ ሠራዊትም አሸንፈው በታተኗቸው ። ይልቁንም ካሌብ እራሱ ያን ከሐዲ ንጉሥ ፊንሐስን ገጠመውና በፈረሱ ላይ እንደ ተቀመጠ በጨበጣ በጦር ወግቶ ገደለውና ወደ ባሕር ገልብጦ ጣለለው። ያም ከሐዲው ንጉሥ ከዚያው ሰጥሞ ሞተ ፤ ሚስቱም በዚሁ ጊዜ ተማረከች ። ከዚያም በኋላ አፄ ካሌብ ዛፋር ፣ ወደምትባለው ወደ ሳባ ከተማ በታላቅ ግርማ ገስግሦ ሄደ ። የከተማውንም ጠባቂዎች አሸንፎ ገብቶ፣ ከተማዋን ያዘ ። ይህም የተደረገው ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በኋላ በአምስት መቶ ሃያ አምስት ዓመተ ምሕረት ላይ ነው ። ፲፬ ፣ ከዚህም በኋላ በዛፋር ከተማ ውስጥ እየተዘዋወረ በክርስቲያኖቹ እልቂት ዕለት ደም በማፍሰስ የተባበሩትን የከሐዲውን የፊንሐስን ሹማምንት እያስፈለገ አስያዘና በአደባባይ በማስገደል በሀገረ ናግራን የተፈጁትን ክርስቲያኖች ደማቸውን በሚገባ ተበቀለ ። የተረፉት ክርስቲያኖችም ከሸሹበትና ከተሸሸጉበት ወደ ቀደመ ቦታቸው ተመለሱ ። ኢትዮጵያዊው ንጉሥ አፄ ካሌብም የድል አድራጊነትን አክሊል እንደ ተቀዳጀ ለእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ መልእክት ላከ ። ሊቀ ጳጳሱም ወደ ቍስጥንጥንያው ንጉሥ ይህንኑ የደስታ መልእክት አስተላለፈና በሁሉም ዘንድ ታላቅ ደስታ ተደረገ በዚያን ጊዜ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አንድ ኤጲስ ቆጶስ ሾሞ ወደ ብሔረ ሳባ ላከ። ኢትዮጵያዊው ንጉሥ አፄ ካሌብም የአይሁዱ ንጉሥ በሚገዛበት በዚያ ግዛት ሁሉ ቤተ ክርስቲያን አሣነፀ ። ለቤተ ክርስቲያኑም መሠረት እራሱ ዓፄ ካሌብ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ሲያስቆፍር ሰነበተ ። ከዚያም ታላቅ በዓል አድርጐ እግዚአብሔርን አመሰገነው ። ያ የክርስቶስ ጠላት አረማዊ ንጉሥ የመዘበራትንና ያጠፋትን ቤተ ክርስቲያን በናግራን ሀገር ላይ እንደገና አሣነፀ ። ከሳባ ሀገር የማረከውን ንብረት ገንብና ጌጣ ጌጥ ሁሉ ለቤተ ከርስቲያኗ ክብር ሰጠ ። ከዚያም ለዚያች ለብሔረ ሳባ ስሙ አብርሃ የሚባል ብልህና ዐዋቂ ሰው መርጦ ሾመላቸው ። ቀጥሎም ገዥውን አብርሃንና ኤጲስ ቆጶሱን የሚጠብቁ ዓሥር ሺህ የጦር ሠራዊት መደበላቸው ። ከዚህ በኋላ ወደ ሀገሩ ወደ አክሱም በፍጹም ደስታና ፍሥሐ በድል አድራጊነት በሰላም ተመልሶ ገባ ። የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ የክርስቲያን አምላካቸው እግዚአብሔር በዚህ ኃያልና ተጋዳይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ በዓፄ ካሌብ እጅ ያደረገውን ድንቅ ሥራ ተመልከቱ። ይህ ዓፄ ካሌብ የአክሱምን መንግሥት የጥንት ግዛቱን በድል አድራጊነት በማስመላሱ የታወቀ አስፈሪና ገናና ንጉሥ ሆኗልና ። ይልቁንም በናግራን የተፈጁትን ክርስቲያኖች ደም በመበቀሉ በእስክንድርያ በቍስጥንጥንያ በአንጾኪያና በሮም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ ኀዘናቸው ወደ ደስታ እንዲለወጥ አድርጓልና። ይህ አማናዊ ንጉሥ ከዓረብ ሀገር ፈጽሞ ሊጠፋ የነበረውን የክርስትና አምልኮ ወደ ጥንት ቦታው መልሶ አቃናው። በቃል ኪዳን ጓደኝነት አንድ ሆነው በነበሩት በአይሁድና በፋርስ ሕዝብ ላይ አደጋ ጥሎ ከዐረብ አገር ግዛታቸውን አስወግዶ ክብራቸውን አሳንሶ እነሱንም አባሮ የራሱን አስተዳደር ተክቶና ገናንነቱን አሳውቆ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት አደላደለ ። ስለዚህ ይህ ታላቅ የኢትዮጵያ [[ንጉሠ ነገሥት]] ዓፄ ካሌብ በምሥራቅ በቍስጥንጥንያና በአረቦችም በቤተ መንግሥቱም በቤተ ክህነቱም በሁሉም ዘንድ ታላቅ ስመ ጥርና ሰፊ ታሪክ ያለው ሆነ ። ክብሩም ከተጋዳዮች ቅዱሳንና ከታላላቅ ሰማዕታት ክብር ጋር የተካከለ ሆነ ። ስለዚህም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመታሰቢያውን በዓል በጥልቅ ስሜት ታከብራለች ። የምታከብረውም የኛ ቤተ ክርስቲያን ብቻ አይደለችም ። ነገር ግን የሮማም ቤተ ክርስቲያን የመታሰቢያውን በዓል ከሌሎቹ አሸናፊዎች ሰማዕታት በዓል ጋር በማስተካከል በጥቅምት ሃያ ሰባት ቀን በታላቅ ክብርና በብዙ ደስታ ታከብረዋለች እንጂ ==መንፈሳዊ ብቃት== የኢትዮጵያው ንጉሥ አፄ ካሌብ በናግራን ሀገር ጦርነት ድልን ተቀዳጅቶ ከተመስሰ በኋላ ኃይልና መጠጊያ ረዳቴና አዳኜ የሚሆን እግዚእብሔርን ምን አድርጌ ላስደስተው ሲል አሰበና የዚህን ዓለም መንግሥት ተድላ ደስታ ንቆ ልብሰ መንግሥቱን አውልቆ አንዲት የውሃ መንቀልና አንዲት ምንጣፍ ብቻ ይዞ አባ ጰንጠሌዎን ገዳም አጠገብ ከሚገኝ ዋሻ ወስጥ ገብቶ በአባ ጰንጠሌዎን እጅ መንኩሶ ለመቀመጥ ወሰነ ። አባ ጰንጠሌዎንንም አመንኵሰኝ አለውና የመላእክትን አስኬማ አልብሶ አመነኰሰው ። ዳግመኛም ከዋሻ ወይም ከገዳም ወጥቶ ዓለምን በዓይኑ ላለማየት ማለ ቃል ኪዳንም ገባ። ቤተ መንግሥቱን ለቆ ወደ ምናኔ በሄደበት ጊዜ ዋጋው እጅግ የከበረውንና በነገሠ ጊዜ የጫነውን የወርቅ ዘውዱን ከጌታችን አንቀጸ መቃብር ላይ ይሰቅልለት ዘንድ ከአደራ ደብዳቤ ጋራ ለኢየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳስ ለአባ ዮሐንስ ላከለት። ዳግመኛም ንጉሥ ዓፄ ካሌብ አባቴ ሆይ በአንተ ጸሎት በእግዚአብሔር ቸርነት ከጦርነቱ በሰላም ተመልሻለሁ አሁንም የክርስቶስን አርዑተ መስቀል ተሽክሜአለሁና እግዚአብሔር ለፍጻሜው ያብቃህ እያልክ ስለኔ ጸልይልኝ ሲል ወደ አባታችን ወደ አቡነ አረጋዊ ላከበት ። ስለዚህም ነገር አባታችን አቡነ አረጋዊ በጣም ተደስቶ ልጄ ሆይ መልካሙን የበለጠውን አድርገሃል። አሁንም እግዚአብሔር የፈቀድከውን ነገር ሁሉ ይፈጽምልህ በለው አለው። መልክተኛውም ይህን ከሰማ በኋላ ከአባታችን ከአቡነ አረጋዊ ዘንድ በረከትን ተቀብሎ ወደ መጣበት ተመልሶ ሄደ። ኢትዮጵያዊው ንጉሥ ዓጼ ካሌብ ይህን ዓለም በመናቅ በበረኃ በዋሻ ዐሥራ ሁለት ዓመት በጾምና በጸሎት በብዙ ተጋድሎ ሲኖር በግንቦት ሃያ ቀን ዐርፎ እስከ ዘለዓስሙ ድረስ የማያልፍ [[ሰማያዊ]] ክብርን ወረሰ ። የተወደዳችሁ ወንድሞች ጻድቅና ትሑት የሚሆን የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዓፄ ካሌብ በፈጣሪው በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ያደረገውን ድንቅ ሥራ እስኪ ተመልከቱ ። የሱና የፈጣሪውን ጠላቶች ዓላውያን ነገሥታት ባጠፋና የጦር ኃይላቸውን በደመሰሰ ጊዜ በኃይሉ አልተመካምና። ከጦር ሜዳም በድል አድራጊነት በተመለሰ ጊዜ ጐልያድን እንደ ገደለ እንደ ዳዊት ዘፋኞች ይዘፍኑለት ወይም ያሞግሱት ዘንድ አልወደደም። ነገር ግን የዚህን ዓለም መንግሥት ንቆ ወደ ምድረ በዳ ወይም በረሃ ገብቶ በትንሽ ዋሻ ውስጥ መኖርን ወደደ እንጂ ። ሎጥ ከሰዶምና ከገሞራ በሚወጣበት ጊዜ መላእክት እስኪያቻኩሉት ድረስ ወዲያ ወዲህ በማለት ለመዘግየት አልፈለገም ። የጨው ዓምድ እንደሆነችው እንደ ሎጥ ሚስትም ክብሩን በማሰብ ፊቱን ወደ ኋላው አልመለሰም ። እንግዲሀ ከኢትዮጵያዊው ንጉሠ ነገሥት ከካሌብ በስተቀር በሚታየው ክብር የማይታየውን ክብር ለውጦ በቆራጥነት ይህን ዓለም ንቆ ሁለተኛ ላለመመለስ ወደፊት ገሥግሶ በረኃ የገባ ማነው እሱ? እኛም እግረ ኅሊናችንን በቀና ጐዳና ይመራልን ዘንድ እግዚአብሔርን እንለም ነው ። ርስተ ወመንግሥተ ሰማያትንም ለመውረስ ዕድል ፈንታችንን ከቅዱሳኖቹጋር ያድርግልን ለዘለዓለሙ አሜን ። ivp8pos0ugx7tmbg8a7grw5jbhgr5jq አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት 0 54941 385933 385827 2025-06-27T06:01:21Z CommonsDelinker 186 ፋይሉ «Anbessa_double_decker.jpg» ከCommons ምንጭ በ[[c:User:Krd|Krd]] ዕጅ ጠፍቷል! ምክንያቱም፦ No license since 19 June 2025 385933 wikitext text/x-wiki {{መረጃ ሳጥን አውቶቡስ ትራንስፖርት|name=|logo=|logo_size=|logo_alt=|image=|image_size=|alt=|image_caption=|former_name=|parent=|founded=|commenced=|ceased=|defunct=|headquarters=|locale=|service_area=|service_type=|alliance=|routes=|stops=|destinations=|hubs=|stations=|lounge=|depots=|fleet=|ridership=|annual ridership=|fuel_type=|operator=|ceo=|leader_type=|leader=|website=|map=|map_state=|map_name=}}{{መረጃ ሳጥን አውቶቡስ ትራንስፖርት}}'''አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት''' በ[[አዲስ አበባ]] ፣ [[ኢትዮጵያ]] በመንግስት ባለቤትነት የሚተዳደር ከከተማ አውቶቡስ የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ሰጭ ድርጅት ነው። == '''ስያሜ''' == አንበሶች በድርጅቱ ምስረታ ወቅት ለነበረው ንጉሣዊ ሥርዓት ትልቅ ግምት ስለነበራቸው ብዙ ተቋማት በስማቸው ይሰየሙ ነበር። አንበሳ ከተመሰረተ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በአቶ ተፈሪ ሻሞ ነበር ስያሜውን ያገኘው። ይሁንና በ2015 ከ80 ዓመታት አገልግሎት በኋላ ድርጅቱ ስያሜውን በመተው "የከተማ አውቶቡስ" ተብሏል። ሆኖም ነባር ተሽከርካሪዎች በውጫዊ ገጽታቸው ላይ አሁንም ስሙንና አርማውን አልቀየሩም። == '''ታሪክ''' == አንበሳ ሥራ የጀመረው ጣሊያኖች ኢትዮጵያን ከወረሩ በኋላ የተዉትን የጭነት መኪናዎች በሞደፊክ በመለወጥ ነው። እስከ 1948 ዓ.ም ድረስ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ሲሰራ ቆይቶ የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት በሚል በንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ በአንዳንድ የመንግሥት ኩባንያዎች እና በንጉሣዊ ቤተሰብ አባላት ባለቤትነት እንደ አክሲዮን ማኅበር በይፋ ተጀመረ። 40 ጣሊያናዊ አሽከርካሪዎችና መካኒኮች ከ80 ኢትዮጵያውያን ሰልጣኞች ጋር ነበሩት። የመጀመሪያው የአንበሳ አውቶቡሶች ቀለም ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት በመነሳት አረንጓዴና ቢጫ የነበረ ሲሆን ሁለት መስመሮች ብቻ ነበሩት፡- እነዚህም :- * '''መስመር 2:''' ፒያሳ እስከ ገነት ሆቴል * '''መስመር 4:''' ሲኒማ ኢትዮጵያ እስከ ካዛንቺስ ነበሩ። በድርጅቱ ለረጅም ጊዜ ሲያገለግል የነበረው አንበሳ ሲዘልል የሚያሳየው አርማ የተነደፈው በጣሊያናዊ አርቲስት ነው። በድጋሚ የቀለማት ማሻሻያ፣ አንበሳ ቀለሙን አሁን ወዳለው ቢጫና ቀይ ለውጧል፤ ይህም ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የታችኛው ሁለት ቀለማት ላይ የተመሠረተ ነው። ምንም እንኳን አንዳንዶች ይህ የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ መለያን መሠረት ያደረገ ነው ብለው ቢከራከሩም። በ1974 ዓ.ም የደርግ ወታደራዊ መንግሥት የአክሲዮን ማኅበሩን በመበተን ድርጅቱን ወደ መንግሥት ይዞታነት አዛወረው። በ1991 ዓ.ም ከደርግ ውድቀት በኋላ ኢህአዴግ እንደ ህዝብ ድርጅት በድጋሚ አቋቋመው። በኢህአዴግ አመራር ስር አንበሳ በአገር ውስጥ በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) የተገጣጠሙ አውቶቡሶችን ገዝቷል። ከእነዚህ በአገር ውስጥ ከተገጣጠሙትና የመገጣጠሚያ ፋብሪካው ከሚገኝበት ከተማ ስም በመነሳት "ቢሾፍቱ አውቶቡሶች" በመባል ከሚታወቁት ከ500 በላይ የሚሆኑትን አውቶብሶች ይጨምራል።ምንም እንኳን አንበሳ የሚያገለግለው በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞኖች ብቻ ቢሆንም ከእነዚህ አውቶቡሶች ውስጥ ስምንቱ ጂማ ውስጥ ይገኛሉ። በአሁኑ ጊዜ በድርጅቱ ሥር ወደ 1000 የሚጠጉ የከተማ አውቶቡሶች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ ወደ 40 በመቶ የሚሆኑት በቴክኒክ ችግሮች ምክንያት ከአገልግሎት ውጪ ነበሩ። በ2015 አ.ም የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በአንፃራዊነት አዲስና አነስተኛ ከሆነው የመንግሥት አውቶቡስ ድርጅት ከሸገር አውቶቡስ ጋር ተዋሀደ። የተዋሀደው ድርጅትም "ከተማ አውቶቡስ" በመባል ተጠራ፤ ይህም የድርጅቱን ታሪካዊነት የሚሽር እንቅስቃሴ ነው በሚል ከፍተኛ ትችት አስነስቷል።ውህደቱ የአውቶቡሶችን ቀለም ወደ ሙሉ አረንጓዴ መቀየርን ያካተተ ቢሆንም ተግባራዊ አልሆነም፤ ሆኖም ከሁለቱም ኦፕሬተሮች የተገኙ አውቶቡሶች ከ2017 ዓ.ም. ጀምሮ ከመዋሃዳቸው በፊት የነበረውን የመጀመሪያውን ቀለምና ስም በውጫዊ አካላቸው ላይ ይዘዋል። ውህደቱን ተከትሎ ከድርጅቱ ወደ 400 የሚጠጉ ሠራተኞችን በዘፈቀደ ከሥራ መሰናበታቸው ውዝግብ አስነስቷል።[[ስዕል:Anbessa Bus.JPG|thumb|ዳፍ 2105 የአንበሳ አውቶብስ ተሽከርካሪ|411x411px]] == '''ተሽከርካሪዎች''' == === የድሮ === * ፊያት ትሬንታ-ኳትሮ የጭነት መኪናዎች * ቢአማክስ የመርሴዲስ አውቶቡሶች፣ * ታታ አውቶቡሶች * ኢካሩስ አውቶቡሶች * ቮልቮ አውቶቡሶች * መርሴዲስ ጆንክሄር * ዳፍ ቤርክሆፍ ጆንክሄር * ሁዋንግሃይ ቢሾፍቱ [[ስዕል:Anbessa bus newer.jpg|thumb|ዩቶንግ ZK6126HG አንበሳ አውቶብስ ስታዲየም ተርሚናል አካባቢ|left]] === የአሁን === ከ2012 ጀምሮ አብዛኛዎቹ ተሽከርካሪዎች ደረጃ አልባ፣ ባለ ፎቅ እና መካከለኛ ወለል ዲዛይን ያላቸው የዩቶንግ አውቶቡስ ሞዴሎች ናቸው። ድርጅቱ ታሪካዊ አውቶብሶችን ለቅርስነት የሚያስቀምጥበት አሰራር የለውም። == '''መስመሮች''' == ድርጅቱ በዋና ከተማዋና ዙሪያዋ በ172 መስመሮች ይሰራል። ከድርጅቱ ጋር የተዋሀደው ሸገር አውቶቡስ የአንበሳን መስመሮች ለመከተል ቀድሞ የነበረውን የነበረውን መስመሮች ትቷል። == በተጨማሪም ይመልከቱ == * ትራንስፖርት በአዲስአበባ * ኮንትራት ታክሲ == ዋቢዎች == {{Reflist}} 0nwz52g9kr0f4wjl3jsa5nx5m1srp31