ውክፔዲያ
amwiki
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8C%88%E1%8C%BD
MediaWiki 1.47.0-wmf.15
first-letter
ፋይል
ልዩ
ውይይት
አባል
አባል ውይይት
ውክፔዲያ
ውክፔዲያ ውይይት
ስዕል
ስዕል ውይይት
መልዕክት
መልዕክት ውይይት
መለጠፊያ
መለጠፊያ ውይይት
እርዳታ
እርዳታ ውይይት
መደብ
መደብ ውይይት
በር
በር ውይይት
TimedText
TimedText talk
ሞጁል
ሞጁል ውይይት
Event
Event talk
ሊቢያ
0
1628
394797
341791
2026-08-18T05:37:39Z
~2026-45180-36
60178
394797
wikitext
text/x-wiki
{{የሀገር መረጃ|
ስም = ሊቢያ|
ሙሉ_ስም = የሊቢያ መንግሥት (State of Libya)|
ባንዲራ_ሥዕል = Flag of Libya.svg|
ማኅተም_ሥዕል = The emblem on the passport of Libya.svg|
መዝሙር = [[ሊቢያ ሊቢያ ሊቢያ]]
"ليبيا ليبيا ليبيا"|
ካርታ_ሥዕል = Libya in its region.svg|
ዋና_ከተማ = [[ትሪፖሊ]]|
ብሔራዊ_ቋንቋ = [[አረብኛ]]|
የመንግስት_አይነት = [[የሽግግር መንግሥት]]|
የመሪዎች_ማዕረግ = የፕሬዝዳንታዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር
[[ጠቅላይ ሚኒስትር]]|
የመሪዎች_ስም = [[ሞሐመድ አል-መንፊ]]
[[አብዱል ሐሚድ ድቤባ]]|
ታሪካዊ_ቀናት = ፫ የካቲት ፲፱፻፴፱ ዓ.ም.
(10 February 1947 እ.ኤ.ኣ.)
፲፬ ታኅሣሥ ፲፱፻፵፬ ዓ.ም.
(24 December 1951 እ.ኤ.ኣ.)|
ታሪካዊ_ክስተቶች = ነጻነት ከ[[ጣልያን]]
የነጻነት አዋጅ (ከትምክህት አስተዳደር)|
የመሬት_ስፋት = 1,759,541|
የመሬት_ስፋት_ከዓለም = 16|
የሕዝብ_ብዛት_ግምት_ዓመት = 2022 እ.ኤ.አ.|
የሕዝብ_ብዛት_ግምት = 7,137,931|
የሕዝብ_ብዛት_ከዓለም = 108|
የገንዘብ_ስም = የሊቢያ ዲናር|
ሰዓት_ክልል = +2|
የስልክ_መግቢያ = 218|
ከፍተኛ_ደረጃ_ከባቢ = .ly}}
'''ሊቢያ''' (በ[[አረብኛ]]: ليبيا) በይፋ '''የሊቢያ መንግሥት''' በሰሜን [[አፍሪካ]] የምትገኝ ሀገር ስትሆን፣ በሰሜን ከ[[ሜድትራኒያን ባሕር]]፣ በምሥራቅ ከ[[ግብፅ]]፣ በደቡብ ምሥራቅ ከ[[ሱዳን]]፣ በደቡብ ከ[[ቻድ]] እና [[ኒጄር]]፣ እንዲሁም በምዕራብ ከ[[አልጄሪያ]] እና [[ቱኒዚያ]] ጋር ትዋሰናለች።
በ1.8 ሚሊዮን ካሬ ኪ.ሜ. የቆዳ ስፋት፣ ሊቢያ በአፍሪካ እና በአረቡ ዓለም አራተኛዋ ትልቋ ሀገር ስትሆን፣ በዓለም ደግሞ 16ኛ ደረጃን ትይዛለች። ዋና ከተማዋ እና ትልቋ ከተማዋ [[ትሪፖሊ]] ስትሆን፣ ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ሕዝብ ውስጥ ከፍተኛው ቁጥር የሚኖረው እዚያው ነው። አብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል በሰሃራ በረሃ የተሸፈነ ነው።
የሊቢያ ዋነኛ የኢኮኖሚ ምንጭ የነዳጅ ዘይት ሲሆን፣ በዓለም 10ኛውን ትልቁን የተረጋገጠ የነዳጅ ክምችት ይዛለች። ይፋዊ ቋንቋዋ [[አረብኛ]] ሲሆን፣ አብዛኛው ሕዝብ የእስልምና እምነት ተከታይ ነው።
ከታሪክ አኳያ የተለያዩ ግዛቶች (እንደ ሮማውያን፣ ግሪኮች፣ ኦቶማን ቱርኮች እና ጣልያኖች) ሊቢያን አስተዳድረዋል። አገሪቱ ከጣልያን ቅኝ ግዛትነት በ፲፱፻፴፱ ዓ.ም. (1947 እ.ኤ.አ.) ነጻነቷን ያወጀች ሲሆን፣ በተባበሩት መንግሥታት ድጋፍ ደግሞ ታኅሣሥ ፲፬ ቀን ፲፱፻፵፬ ዓ.ም. (24 December 1951 እ.ኤ.አ.) ሙሉ የነጻነት አዋጅ አጽድቃለች። በ1969 እ.ኤ.አ. በ[[ሞአመር ጋዳፊ]] መሪነት የተካሄደው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ንጉሣዊውን ሥርዓት በማስወገድ አገሪቱን ለ42 ዓመታት ያህል አስተዳድሯል። ሞአመር ጋዳፊ «የተባበሩት የአፍሪካ አገራት» የሚል ጽንሰ-ሀሳብን በብርቱ ያራምዱ ነበር።
በ፳፻፫ ዓ.ም. (2011 እ.ኤ.አ.) በተነሳው የሊቢያ ሕዝባዊ አብዮት (የመጀመሪያው የእርስ በርስ ጦርነት) የጋዳፊ መንግሥት ከወደቀ በኋላ፣ ሀገሪቱ በፖለቲካ አለመረጋጋት እና በሽግግር መንግሥታት አስተዳደር ውስጥ ትገኛለች። በአሁኑ ወቅት ሊቢያ በሽግግር መንግሥት የምትመራ ሲሆን፣ ሀገሪቱ ወደ ቋሚ ሕገ-መንግሥትና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማምራት በሂደት ላይ ትገኛለች።
{{በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ አገሮች}}
{{መዋቅር-መልክዐምድር}}
[[መደብ:ሊቢያ|*]]
16rut4xnai6012ndbgtv6q308yu7pi0
ጋምቤላ ሕዝቦች ክልል
0
2415
394799
371108
2026-08-18T07:07:08Z
~2026-45180-36
60178
394799
wikitext
text/x-wiki
{{የቦታ መረጃ
| ስም = የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
| የቦታ_ዓይነት = [[የኢትዮጵያ ክልሎች|ክልል]]
| ይፋ_ስም = ጋምቤላ ክልል
| ስዕል = Gambela in Ethiopia.svg
| ስዕል_መግለጫ = የጋምቤላ ክልልን በቀይ የሚያሳይ የኢትዮጵያ ካርታ
| ባንዲራ = Flag of the Gambella Region.svg
| አርማ =
| ክፍፍል_ዓይነት = አገር
| ክፍፍል_ስም = [[ኢትዮጵያ]]
| ምሥረታ_ስም = የተመሰረተበት
| ምሥረታ_ቀን = ፲፱፻፹፯ ዓ.ም.
(1995 እ.ኤ.አ.)
| መቀመጫ_ዓይነት = ርዕሰ ከተማ
| መቀመጫ = [[ጋምቤላ (ከተማ)|ጋምቤላ]]
| መሪ_ማዕረግ = ርዕሰ መስተዳድር
| መሪ_ስም = አለሚቱ ኡሞድ
| መሪ_ማዕረግ2 = ምክትል ርዕሰ መስተዳድር
| መሪ_ስም2 = ዶ/ር ጋትሏክ ሮን
| ቦታ_ጠቅላላ = 29,782
| ሕዝብ_ጠቅላላ = 385,997<ref name="csa">{{cite web|title=፳፻፬ ዓ.ም. ብሔራዊ ስታቲስቲክስ|url=http://www.csa.gov.et/images/documents/pdf_files/nationalstatisticsabstract/2011/2011%20population.pdf|publisher=ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ|accessdate=ሰኔ ፳፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.|archivedate=2015-09-23|archiveurl=https://web.archive.org/web/20150923211414/http://www.csa.gov.et/images/documents/pdf_files/nationalstatisticsabstract/2011/2011%20population.pdf}}</ref>
| ሕዝብ_ዓመት = 2011 እ.ኤ.አ.

'''የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት''' (ወይም '''ጋምቤላ ክልል''') በደቡብ ምዕራብ [[ኢትዮጵያ]] ከሚገኙት ክልሎች አንዱ ነው። ዋና ከተማው [[ጋምቤላ (ከተማ)|ጋምቤላ]] ነው። ክልሉ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ ከ[[ደቡብ ሱዳን]]፣ በሰሜን እና በምሥራቅ ከ[[ኦሮሚያ ክልል]]፣ እንዲሁም በደቡብ እና በደቡብ ምሥራቅ ከ[[ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል]] ጋር ይዋሰናል።
የጋምቤላ ክልል ወደ 29,782 ካሬ ኪ.ሜ. የቆዳ ስፋት ሲኖረው፣ በአብዛኛው ዝቅተኛና ሞቃታማ የአየር ንብረት አለው። ክልሉ በተፈጥሮ ሀብት፣ በተለይም በውኃ፣ በደኖች፣ በእርሻ መሬት እና በነዳጅ ሀብት የበለፀገ መሆኑ ይታመናል። በአካባቢው የሚገኙት ትላልቅ ወንዞች (እንደ [[ባሮ ወንዝ|ባሮ]]፣ [[አኮቦ ወንዝ|አኮቦ]]፣ እና [[ጊሎ ወንዝ|ጊሎ]]) ለግብርና፣ ለአሳ ማስገር እና ለውሃ ትራንስፖርት ከፍተኛ ጠቀሜታ አላቸው። በአካባቢው ከሚገኘው ሰፊው የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ የበርካታ የዱር አራዊትና አእዋፋት መገኛ ነው።
== የሕዝብ ስብጥር ==
የጋምቤላ ክልል በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች በጋራ የሚኖሩበት አካባቢ ሲሆን፣ ክልሉን በዋናነት የመሠረቱት አምስት አገር በቀል ብሔረሰቦች የሚከተሉት ናቸው፦
* [[ኑዌር]] (Nuer)
* [[አኝዋክ]] (Anywaa)
* [[ማጃንግ]] (Majang)
* [[ኦፖ]] (Opo)
* [[ኮሞ]] (Komo)
ከእነዚህም በተጨማሪ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የመጡ የተለያዩ ብሔረሰቦች (እንደ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ከፋ፣ ወዘተ) በክልሉ በስፋት ይኖራሉ። አብዛኛው የክልሉ ሕዝብ በግብርና፣ በከብት እርባታ፣ እንዲሁም በአሳ ማስገር ይተዳደራል።
{{የኢትዮጵያ_መረጃ}}
[[መደብ:የኢትዮጵያ ክልሎች]]
[[መደብ:ጋምቤላ ክልል]]
== ማመዛገቢያዎች ==
{{reflist}}
57hklestgf8unnoijpq43o662rtqpae
ሳን ቶሜ እና ፕሪንሲፔ
0
3316
394800
373551
2026-08-18T08:12:14Z
~2026-45180-36
60178
394800
wikitext
text/x-wiki
{{የሀገር መረጃ|
ስም = ሳን ቶሜ እና ፕሪንሲፔ|
ሙሉ_ስም = የሳን ቶሜ እና ፕሪንሲፔ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
(República Democrática de São Tomé e Príncipe)|
ባንዲራ_ሥዕል = Flag of São Tomé and Príncipe.svg|
ማኅተም_ሥዕል = Coat of arms of São Tomé and Príncipe.svg|
መዝሙር = ''Independência total'' (ፍጹም ነጻነት)|
ካርታ_ሥዕል = Sao Tome and Principe in its region.svg|
ዋና_ከተማ = [[ሳን ቶሜ]]|
ብሔራዊ_ቋንቋ = [[ፖርቱጊዝኛ]]|
የመንግስት_አይነት = ፕሬዚዳንታዊ ሪፐብሊክ|
የመሪዎች_ማዕረግ = [[ፕሬዚዳንት]]
[[ጠቅላይ ሚኒስትር]]|
የመሪዎች_ስም = [[ካርሎስ ቪላ ኖቫ]]
[[ፓትሪስ ትሮቭዋዳ]]|
ታሪካዊ_ክስተቶች = ነጻነት ከ[[ፖርቱጋል]]|
ታሪካዊ_ቀናት = ፭ ሐምሌ ፲፱፻፷፯ ዓ.ም.
(12 July 1975 እ.ኤ.አ.)|
የመሬት_ስፋት = 1,001|
የመሬት_ስፋት_ከዓለም = 171|
የሕዝብ_ብዛት_ግምት_ዓመት = 2021 እ.ኤ.አ.|
የሕዝብ_ብዛት_ግምት = 223,107|
የሕዝብ_ብዛት_ከዓለም = 178|
የገንዘብ_ስም = የሳን ቶሜ እና ፕሪንሲፔ ዶብራ (Dobra)|
ሰዓት_ክልል = +0 (ግሪንዊች አማካይ ሰዓት)|
የስልክ_መግቢያ = +239|
ከፍተኛ_ደረጃ_ከባቢ = .st}}
'''ሳን ቶሜ እና ፕሪንሲፔ''' (በ[[ፖርቱጊዝኛ]]: São Tomé e Príncipe) በይፋ '''የሳን ቶሜ እና ፕሪንሲፔ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ''' በመካከለኛው [[አፍሪካ]] ምዕራባዊ የባህር ዳርቻ (በጊኒ ባሕረ ሰላጤ) የምትገኝ የደሴት ሀገር ናት።
ሀገሪቱ በዋናነት በሁለት ደሴቶች የተዋቀረች ሲሆን፣ እነሱም ሳን ቶሜ እና ፕሪንሲፔ በመባል ይታወቃሉ። እነዚህ ደሴቶች እርስ በርሳቸው በ140 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ከጋቦን የባህር ዳርቻ ደግሞ ከ225 እስከ 250 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛሉ። ከ[[ሲሸልስ]] ቀጥሎ በአፍሪካ ሁለተኛዋ አነስተኛ ሀገር ስትሆን፣ በዓለም ላይ ካሉ ሉዓላዊ አገራት መካከልም በቆዳ ስፋቷ እጅግ አነስተኛ ከሚባሉት ተርታ ትመደባለች። የሀገሪቱ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 1,001 ካሬ ኪሎ ሜትር ነው።
== ታሪክ ==
ደሴቶቹ በ15ኛው ክፍለ ዘመን (በ1470 አካባቢ) በፖርቱጋል አሳሾች እስከተገኙበት ጊዜ ድረስ ሰው አልነበረባቸውም። በኋላም በፖርቱጋል ቅኝ ግዛት ስር የወደቁ ሲሆን፣ ለአትላንቲክ የባሪያ ንግድ ማዕከል በመሆን አገልግለዋል። በተጨማሪም ደሴቶቹ በስኳር፣ በካካዎ እና በቡና እርሻዎች በስፋት ይታወቁ ነበር። የሀገሪቱ ሕዝብ የፖርቱጋላውያን ሰፋሪዎች እና ከአፍሪካ አህጉር የመጡ ባሮች ዝርያ ድብልቅ ነው።
ከብዙ መቶ ዓመታት የፖርቱጋል ቅኝ ግዛት በኋላ፣ አገሪቱ ሐምሌ ፭ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. (12 July 1975 እ.ኤ.አ.) ነጻነቷን ተቀዳጀች። ከ1990ዎቹ ጀምሮ ሀገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን በመከተል ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር በማድረግ በአፍሪካ ከተረጋጉ አገራት አንዷ ሆናለች።
== ማህበረሰብ እና ኢኮኖሚ ==
ዋና ቋንቋዋ እና ብሔራዊ የሥራ ቋንቋዋ [[ፖርቱጊዝኛ]] ነው። አብዛኛው የሀገሪቱ ሕዝብ (ከ220,000 በላይ) በሳን ቶሜ ደሴት ላይ የሚኖር ሲሆን፣ አብዛኛው የክርስትና እምነት (በተለይም የሮማን ካቶሊክ) ተከታይ ነው። የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በዋናነት በግብርና (በተለይም የካካዎ ኤክስፖርት)፣ በአሳ ማስገር፣ እና በማደግ ላይ ባለ የቱሪዝም ዘርፍ ላይ የተመሰረተ ነው።
{{በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ አገሮች}}
{{መዋቅር-መልክዐምድር}}
[[መደብ:መካከለኛ አፍሪቃ]]
[[መደብ:ሳን ቶሜ እና ፕሪንሲፔ]]
[[መደብ:የአፍሪካ ሀገራት]]
sghcjiwoggn217q1vduczzsoi81yldy
ስንዱ ገብሩ
0
8561
394798
377344
2026-08-18T07:06:29Z
~2026-45180-36
60178
394798
wikitext
text/x-wiki
[[ስዕል:SeneduGebru1.jpg|right|180px|ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ ]]
'''ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ'''የመጀመሪያዋ ሴት የፓርላማ ተመራጭ፣ የጦር አርበኛ፣ ፀሐፊ- ተውኔት፣ ደራሲ፣ የመጀመሪያዋ ሴት ዲፕሎማት የነበሩት እና [[ሚያዝያ 12|ሚያዝያ ፲፪]] ቀን [[2001|፳፻፩]] ዓ/ም በ፺፫ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩን የክብርት ዶክቶር፣ ወይዘሮ ስንዱ ገብሩን ማንነት የሚዘክር “ዝክረ - ስንዱ ገበሬ”፣ በሚል ዝግጅት በ[[እቴጌ መነን]] ትምህርት ቤት በኢትየጽያ የሴቶች ማኅበራት ቅንጅት (ኢሴማቅ)፣ ከኢትዮጵያ ሴት ደራሲያን ማኅበር፣ ከኢትዮጵያ ሴት መገናኛ ብዙኀን ማኅበር፣ ከኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበረና፣ ከጾታዊ ጥቃት መከላከያ ማኅበር ጋር በትብብር የተዘጋጀ ዝክር ተከናውኗል።
==ልደትና የወጣትነት ዘመናት==
ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ በ[[ሸዋ]] ክፍለ ሀገር በመናገሻ አውራጃ በ[[አዲስ ዓለም]] ከተማ [[ጥር 6|ጥር ፮]] ቀን [[1908|፲፱፻፰]] ዓ/ም ተወለዱ። አባታቸው ታዋቂው ዲፕሎማት፣ የመጀመሪያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዘደንት፤ ጣሊያኖች ከኢትዮጵያ ከወጡ በኋላ ደግሞ የምክር ቤቱ ፕሬዘደንት የነበሩት በ[[ዳግማዊ ምኒልክ]] ሹመትም የመጀመሪያው የ[[ጎንደር]] ከተማ አስተዳዳሪ የነበሩት [[ከንቲባ ገብሩ]] ደስታ ሲሆኑ ታናሽ እህታቸው ደግሞ የውብዳር ገብሩ (አሁን ታዋቂዋ ሙዚቀኛ እማሆይ ጽጌ ማርያም) ናቸው።
ዕድሜያቸው ለትምህርት በደረሰበት ወቅት እቤታቸው አስተማሪ ተቀጥሮላቸው የ[[አማርኛ]]ን ትምህረት ከፊደል መቁጠር እስከ ዳዊት መድገም በቤታቸው ተማሩ። ከዚያም ወደ [[አዲስ አበባ]] ሄደው በ[[ስዊድን]] ሚሲዮን ትምህርት ቤት በመግባት እስከ ስምንተኛ ክፍል ተምረዋል።
[[ከንቲባ ገብሩ]] ወጣቷን ስንዱ ገብሩን እያስከተሉ ወደ ቤተ መንግሥትም ሆነ ሌላ ሥፍራዎች ይወስዷቸው እንደነበረና ከጊዜው [[አልጋ ወራሽ]] ተፈሪ መኮንንም ጋር እንዳስተዋዋቋቸው ተዘግቧል። አልጋ ወራሹም የወጣቷን ብልህነትና ትጋት በማድነቅ ወደ ፈረንጅ አገር ተልከው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ባዘዙት መሠረት ወይዘሮ ስንዱ በ[[1921|፲፱፻፳፩]] ዓ/ም (ፊታውራሪ አመዴ በ፲፱፻፲፱ ዓ/ም ይላሉ) ወደ [[ስዊስ]] ለትምህርት ቢሄዱም ኑሮው ስላልተመቻቸውና ትምህርት ይሰጥበት የነበረውን የ[[ጀርመንኛ]] ቋንቋ ስላልወደዱት ወደ [[ፈረንሳይ]] አቅንተው ትምህርታቸውን ቀጠሉ። በመጨረሻም በ[[ስዊስ]] እና በ[[ፈረንሳይ]] ሁለት ትምህርት ቤቶች በመዘዋወር በዲፕሎማ ተመረቁ። እዛው የሕግ ትምህርት ለመቀጠል ጀምረው የነበረ ቢሆንም፤ ፍላጎታቸው ወደ ሥነ-ጽሑፍ በማዘንበሉ በአጠቃላይ ለአምስት ዓመታት እዛው ተምረው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።
ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱም በ[[አዲስ አበባ]] በቅዱስ ጊዮርጊስ ትምህርት ቤት ውስጥ የፈረንሳይኛ ቋንቋን፣ ሀይጅን፣ ቁጥርንና የአማርኛ ድርሰት አጻጻፍን ማስተማር ጀመሩ። በዚህ ሁኔታ አንድ ዓመት እንደቆዩ ለብላታ [[ሎሬንሶ ታዕዛዝ]] ተዳሩና ባለቤታቸው የ[[ሐረርጌ]] ክፍለሀገር አስተዳዳሪ ሆነው በመሾማቸው ወደዚያው ከባለቤታቸው ጋር አቀኑ። ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላም ብላታ ሎሬንሶ የፍርድ ቤት ሹምና የዜና ስርጭት ኃላፊ ሆነው በመሾማቸው ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ አብረዋቸው ወደ [[አዲስ አበባ]] ተመለሱ።
==የፋሺስት [[ኢጣልያ]] ወረራ ዘመናት==
ፋሺስቶች ኢትዮጵያን በወረሩ ጊዜ ንጉሠ ነገሥቱ [[ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ]] ወደ [[ዩናይትድ ኪንግደም|እንግሊዝ]] ሀገር ሲሰደዱ ብላታ [[ሎሬንሶ ታዕዛዝ]]ም አብረው ከጃንሆይ ጋር ሄዱ። ወይዘሮ ስንዱ ግን ከቤተሰቦቻቸው ጋር እና [[ሆለታ]] ውስጥ ከሚገኙ ወደ መቶ የሚጠጉ የጦር መኮንኖች ጋር ተቀላቅለው ፋሺስቶችን ለመፋለም ወደ ቦሬ ሄዱ። እዚያም የመትረየስ አተኳኮስ ትምህርት ተማሩ። ወደ [[ነቀምት]] በመሄድም ሕዝብን እየሰበሰቡ ስለ ነፃነት ማስተማሩን ተያያዙት። በዚህ ወቅት በባንዳዎች ጠቋሚነት በፋሽስት እጅ ከመውደቅ ለጥቂት አምልጠው [[ጎሬ]] ላይ ከ[[ልዑል ራስ እምሩ]] ጦር ጋር ተቀላቀሉ። ከዚያም በጦርነቱ የሚጎዱ አርበኞችን ለማከም የሚሆን ቀይ መስቀል ለማቋቋም መፈለጋቸውን ለራስ እምሩ አማክረው በተሰጣቸው ፭ መቶ ብር አቋቁመው አርበኞችን መርዳት ጀመሩ። ወዲያው ግን እርሳቸው ተቀላቅለውት የነበረው የጥቁር አንበሳ ጦር ሲመታ በ[[ጣልያን]] ሠራዊት እጅ ተማርከው በእስር ወደ አዲስ አበባ አመጧቸውና የቁም እስረኛ ሆኑ።
[[የካቲት 12|የካቲት ፲፪]] ቀን [[1929|፲፱፻፳፱]] ዓ/ም [[ግራዚያኒ]]ን ለመግደል በተደረገው ሙከራ ወንድማቸው መሸሻ ገብሩ አሉበት በመባል ይታሰሱ ስለነበር ወንድማቸውን ከአደጋ ለማዳን ሲሞክሩ በድጋሚ በፋሺስቶች እጅ ወደቁ። በወቅቱ ግራዚያኒ ይኖርበት የነበረው የ[[ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት]] ውስጥ ታሰሩ። ቀጥሎም ወደ [[አስመራ]]፣ ከዚያ ወደ [[ምጽዋ]] ተወሰዱ። ከምጽዋ ወደብ ሦስት መቶ ወንዶችና ስምንት ሴቶች (እማሆይ ጽጌ ማርያምን ጭምር) ሆነው በመርከብ “አዚናራ” ወደተባለች የኢጣሊያኖች እስር ቤት ተወስደው ዘጠኝ ወራት ታሰሩ።
ከእስር በኋላም ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ በእንደዚህ ያለ ተግባር ላይ እንዳይሰማሩ ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም፤ ማስፈራሪያው ሳይበግራቸው አርበኞችን በግጥም፣ በወኔ ቀስቃሽ ጽሑፎች በማበረታታት፣ መረጃ በማቀበል፣ መሣሪያ በማዳረስ የጀግንነት ተግባር ፈጽመዋል።
==ከድል በኋላ==
ከድል በኋላ ወይዘሮ ስንዱ ለሁለት ዓመታት [[ደሴ]] ከተማ የሚገኘው የ[[ወይዘሮ ስኂን ትምህርት ቤት]] አስተዳዳሪ በመሆን፣ በኋላም ወደ አዲስ አበባ ተመልሰውም የ[[እቴጌ መነን ትምህርት ቤት]] ምክትል ርዕሰ መምህርነት፣ ከዚያም የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ መምህር ሆነው አገልግለዋል። በእቴጌ መነን ትምህርት ቤት በነበሩበት ወቅት፤ “ኮከብ ያለው ያበራል ገና”፣ “የየካቲት ቀኖች”፣ “የኑሮ ስህተት” የሚሉ ትያትሮችን ሠርተው አቅርበዋል።
==የመጀመሪያዋ ሴት የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባል==
ከ[[1948|፲፱፻፵፰]] ዓ/ም እስከ [[1952|፲፱፻፶፪]] ዓ/ም ድረስ የመጀመሪያዋ የሴት [[የሕግ መምሪያ ምክር ቤት]] አባልና [[የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት]] ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው አገልግለዋል። በዚህ ምክር ቤት አባል በነበሩበት ጊዜ ብቸኛዋ ሴት ከመሆናቸውም ባሻገር የሴቶች እኩልነት በማይከበርበት ጊዜ እና “የወንድ ዓለም” በገነነበት የታሪክ ምዕራፍ የሴቶችን ሰብዓዊ መብት ለማስከበርና እኩልነትን በሕግ ለማስተማመን ብዙ የታገሉ ሴት ነበሩ። ስለዚህ ጊዜ ሁኔታዎች ምስክርነት ከሰጡት በከፊሉ፦

“… የቤተሰብ ሕጉ በእርሳቸው ጊዜ ሲወጣ፣ የመኖሪያ ስፍራ የመምረጥን መብት በተመለከተ ለባል የተሰጠውን መብት ተከራክረው ተቀባይነት ቢያጡም የፍትሕ ብሔር ሕጉ ላይ ሴቶች ባገቡት ወንድ ስም ይጠሩ የሚለውን በመቃወም እንዳይፀድቅ ያደረጉና ያስቀየሩ ሴት ስለሆኑ ቀዳማይት ታጋይ እላቸዋለሁ። …”

ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ፤ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ።

“… የተፈጠሩበትን ዘመን፣ ሁኔታና አካባቢ አልፈው ዓላማቸውን ያሳኩ አንቱ ለተባለላቸው የአገልግሎቶችና የሥራ አይነቶች ከውጊያ እስከ ውሳኔ ሰጪነት በመቀመጥ ፈር ቀዳጅ ናቸው። በተቀመጡበት ሥልጣንም፣ ለተነሱበት ዓላማ ለሴቶች የእኩልነት ጥያቄ የከፈሉት አስተዋጽኦና ተግባራት በታሪክ የዘመኑ ታላቅ ሰው ያደርጋቸዋል …”

ወይዘሮ ሳባ ገብረ መድኅን፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት ዳይሬክተር።
እራሳቸውም በጊዜው የዚሁ ሸንጎ አባል የነበሩት ፊታውራሪ አመዴ ለማ ደግሞ ስለዚህ ጉዳይ ትዝታቸውን ሲያካፍሉን፦

“የፍተሐ ብሔሩ ሕግ ቀርቦ ስንከራከር፣ ምን ይላል ፍትሐ ብሔር ውስጥ ያን ጊዜ ሲወጣ፣ ‘የቤቱ ሹም ባል ይሆናል። ሚስት ለባሏ ታዛዥ መሆን አለባት። እንዲህ እንዲህ የሚል ሴቶችን የሚጫኑ አንቀጾች አሉ። ይሄንን ወይዘሮ ስንዱ የዚያን ጊዜ ቀደም ብለው የነቁ ስለነበረ “እንዴ! ለምን አንድ ጊዜ እኛን ንጉሠ ነገሥቱ እኩል ናችሁ ካሉን በኋላ በእራሳችን ስምምነት እንጂ በሕግ ሴቶችን የሚጨቁን ሕግ መግባት የለበትም” ብለው ተከራከሩ። እሺ ድምጽ ይሰጥበት ሲባል አንድ ሰው ብቻ ደገፋቸው። ተናደዱ። “እናንተ እዚህ ምክር ቤት የመጣችሁ ወንዶች፤ ስትመረጡ ሴትና ወንደ ነበር የመረጣችሁ፣ ግን ልትመክሩ የመጣችሁት ለወንዶች እንጂ ለሴቶች እንዳልሆነ ታዝቤአችኋለሁ። ይህ ዛሬ እናንተ የሰጣችሁት ውሳኔ፣ ከአንድ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ብዙ ሴቶች ገብተው ይገለብጡታል እና ዘለቄታ የለውም።”

ብለው ተናደው ይሄን ተናግረው ወጡ። ይላሉ
ሌላው የዚህ ሸንጎ አባልና ለብዙ ዘመናት የወይዘሮ ስንዱ ጓደና የነበሩት አቶ ጠንክር ተድላ፦ ሴቶችን በተመለከተ ጉዳይ ባል ከሚስቱ እውቀት ውጭ ከ አምሥት መቶ ብር በላይ እንዳይበደር የሚል ሃሣብ አቅርበው በጋለ ስሜት እንደተከራከሩና ውጤቱም ይህ ቁም ነገር ሕግ ለመሆን የበቃ መሆኑን ይመሰክራሉ።
ሌላው ብዙ የተሟገቱበትና ውጤታማ የሆኑበት ጉዳይ በጊዜው ቀርቦ የነበረው ‘እንደ ፈረንጆች’ ተለምዶ የኢትዮጵያም ሴቶች ባል ሲያገቡ የባላቸውን አባት ስም እንዲጠቀሙበት የሚል ያልተሳካ የሕግ ረቂቅ ነበር።
==ሌላ አስተዋጽዖዎች==
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማኅበር ፕሬዝዳንት፣ የሕዝባዊ ኑሮ እድገት ዋና ፀሐፊነትና አስተዳዳሪነት፣ በምዕራብ ጀርመን ለሦስት ዓመት የትምህርት አታሼ በመሆን አገልግለዋል። ወይዘሮ ስንዱ ከአሥር በላይ የግጥምና ልብ ወለድ መጻሕፍት የጻፉ ሲሆኑ ሠላሳ ሁለት ጽሑፎቻቸው በ [[አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ] ይገኛሉ።
==የድርሰት ሥራዎች==
* ኮከብህ ያውና ያበራል ገና
* በግራዚያኒ ጊዜ የየካቲት ቀኖች (፲፱፻፵፯ ዓ/ም)
* የታደለች ህልም (፲፱፻፵፰ ዓ/ም)
* ርእስ የሌለው ትዳር (፲፱፻፵፰ ዓ/ም)
* የኔሮ ስህተት (፲፱፻፵፰ ዓ/ም)
* ከማይጨው መልስ (፲፱፻፵፱ ዓ/ም)
* ፊታውራሪ ረታ አዳሙ (፲፱፻፵፱ ዓ/ም)
የመጀመሪያዋ የሴት ፓርላማ አባል፣ የሴት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ጀግናና ፀረ-ፋሺስት አርበኛ፣ ፀሐፊ ተውኔት፣የመጽሐፍ ደራሲ፣ እና የመጀመሪያዋ የሴት ዲፕሎማት ስንዱ ገብሩ (የክቡር ዶክተር) [[ሰኞ]] [[ሚያዝያ 12|ሚያዝያ ፲፪]] ቀን [[2001|፳፻፩]] ዓ/ም በተወለዱ በ ፺፫ ዓመታቸው ሕይወታቸው አልፎ በ[[መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ]] ቤተ ክርስቲያን ተቀብረዋል።
ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ ላበረከቷቸው አስተዋጽዖዎች የወርቅ ሜዳሊያ፣ የንግሥት ሣባ የወርቅ ኒሻን፣ የቀይ መስቀል የወርቅ ሜዳሊያ እና በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ዘመን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተሰጥቷቸዋል።
==ዋቢ ምንጮች==
* Ethiopia Zare (ሰኞ ግንቦት 3 ቀን 2001 ዓ.ም. May 11, 2009)
* [http://www.webspawner.com/users/yonashailemeskel/] {{Wayback|url=http://www.webspawner.com/users/yonashailemeskel/ |date=20070929083700 }} «History of Ethiopian Theater» በዮናስ ኃይለ መስቀል. ፌብሩዋሪ 20 ቀን 2007 ታይቷል።
* http://www.horizonethiopia.com/index.php?option=com_content&task=view&id=352&Itemid=3&ed=15 (መስከረም ፳፭ ቀን ፳፻፫ ዓ/ም ታይቷል።)
[[መደብ:የኢትዮጵያ ጸሓፊዎች]]
[[መደብ:አርበኞች]]
538f50ag6m3gpvfaz4ndg057m8zju60
ቤንች
0
22397
394794
367351
2026-08-17T12:47:55Z
~2026-45254-95
60166

394794
wikitext
text/x-wiki
==ቋንቋ==
የቤንች ብሔረሰብ ቋንቋ ‹‹[[ቤንችኛ]]›› ሲሆን ከምዕራብ ኦሞአዊ የቋንቋ ቤተሰብ ይመደባል። የብሔረሰቡ አባላት ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ [[አማርኛ]]፣ ካፊኖኖ እና [[ሸኮኛ]] ቋንቋዎችን ይናገራሉ።
==ሕዝብ ቁጥር ==
==መልክዓ ምድር ==
የቤንች ብሔረሰብ አባላት በዋናነነት በዞኑ በሰሜን ቤንች እና በደቡብ ቤንች፣በሸዋ ቤንች ወረዳዎች እንዲሁም በሸኮ እና ጉራፈርዳ ወረዳዎች ውስጥ ይኖራሉ፡፡ ከዞኑ ውጭም የብሔረሰቡ አባላት ኩታ ገጠም በሆኑት በከፋ ዞን በጨና እና ዳቻ ወረዳዎች፣ በሻካ ዞን በየኪ ወረዳ እንዲሁም በአዲስ አበባ ‹‹ጊሚራ›› ሰፈር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ይገኛሉ፡፡ ብሔረሰቡ የሚገኝበት አቀማመጥ ሜዳማ፣ ተራራማ እና ሸለቋማ ሲሆን፤ ደጋማ፣ ቆላማ እና ወይና ደጋ የአየር ንብረት አለው፡፡ የብሔረሰቡ ዋነኛ መተዳደሪያ ጥምር ግብርና ነው፡፡ ከተክሎች፣ ከሥራሥር፣ ከጥራጥሬ፣ ከቅመማቅመም ከአገዳ እህል የሚገኙ ምርቶች ያመርታል፡፡ ቡና ዋና የገቢ ምንጭ ሲሆን፤ ቅመማቅመም፣ ቆዳ እና ሌጦ ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ ናቸው፡፡
== ታሪክ ==
ቤንች ብሔረሰብ በቤንች ማጅ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ስድስት ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ነው፡፡ የብሔረሰቡ አሰያየም ‹‹ቤንችቲያት›› ከተባለው ጥንታዊ የብሔረሰቡ መሪ እንደተወለደ ይነገራል፡፡ ‹‹ታት›› የሚባለው ቃል ‹‹ጌታ›› ማለት ሲሆን ለብሔረሰቡና ለቋንቋው መጠሪያ ነው፡፡
በቤንች ብሔረሰብ በርካታ ጐሳዎች ቢገኙም ከምት፣ ቃም፣ ማንጃ(ባንድ) እና ማኖ(ፋቂ) ዋና ዋናዎቹ ናቸው በሐረሰቡ የራሱ የሆነ ባህላዊ አስተዳደር እና የዳኝነት ሥርዓት ያለው ሲሆን፤ ባህላዊ አስተዳደሩ የሥልጣን እርከን እና የሥራ ኃላፊነት የሚወሰነው በእርከኑ ባሉ ሽማግለዎችና በጎሳ መሪዎች ምርጫ ነው፡፡ ‹‹ከምት›› ከፍተኛ ከበሬታ የሚሰጠው መሪ ነው፡፡ ማንኛውንም ፖለቲካዊ ማኀበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮችን በበላይነት ይመራል፡፡ የባህላዊ አስተዳደሩ ቁንጮ ከእዚህ ጎሣ የሚሾም ሲሆን ‹‹ቤንችያት›› (ከምት) ባላባት ይባላል፡፡ የሚመረጠውም ‹‹ከዛግንድ›› ጎሳ ነው፡፡ የሥልጣን ሽግግሩም የዘር ሀረግን የተከተከለ ሲሆን የመሪዎቹ ወይም የ‹‹ቲያቶት›› ሥልጣን የሚተላለፈው ከ‹‹ቲያቶች›› የመጠሪያ ሚስት ለተወለደ የበኩር ልጅ ነው፡፡ መሪው ልጅ ሳይተካ ከሞተ ወንድሙ ሥልጣኑን ይወርሳል፡፡ ለ‹‹ቲያትነት›› የሚመረጠው ልጅ ወይም ወንድም በቂ ችሎታ ያለው እና ከሌለ ወገን ያልተከቀላቀለ ቤንች መሆን ይጠበቅበታል፡፡
ብሔረሰቡ ግጭቶችን የሚፈታበት የተለያዩ መንገዶች ያሉት ሲሆን፤ ግድያ ከተፈፀመ ወንጀሉ አፈፃፀም ከተጣራ በኋላ በሁለቱ ደመኞች ድንበር ላይ በሬ ታርዶ በደም ይታረቃሉ፡፡ ልጃገረድም ከገዳይ ወገን በካሳ ትሰጣለች፡፡ በብሔረሰቡ መዋሸት፣መሥረቅ፣ዝሙት መፈጸም አጥብቆ የተከለከለ ነው፡፡ ይህን ተግባር የፈጸመ ለቃልቻ ወይፈን ወይም ጊደር ይሰጣል፡፡ ከ1ዐ እስከ 3ዐ ጅራፍም ይገረፋል፤ በእግረሙቅ ይታሠራል፤ ለተወሰኑ ወራትም ለባላባቱ እንዲያደርስ ይደረጋል፡፡
በቤንች ብሔረሰብ የጋብቻ ሥርዓት በቤተሰብ ስምምነት፣በጠለፋ፣በማስኮብለል እና በውርስ ይፈጸማል፡፡ በብሔረሰቡ ሴት ልጅ 15 ዓመት ወንድ ልጅ ደግሞ 2ዐ ዓመት ሲሞላው የጋብቻ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ ባላባቱ እስከ 4ዐ ሚስቶችን ማግባት ሲችል አንጋፋዋ ሚስት ‹‹ጌን›› ትባላለች፡፡
በብሔረሰቡ ከወቅቶች ጋር ተያይዞ ምርት እንዲሰጥ፣ በሽታ እንዲጠፋ፣ ሰላም እንዲሰፍን በዓመት 3 ጊዜ የሚከበሩ በዓላት አሉ፡፡ በዓላቶቹ በቃልቻዎችና በባለአባቱ የሚመሩ ሲሆን፤ቦርዴ ተጠምቆ ልዩ ልዩ መልክ ያላቸው ዶሮዎች እና ከ5ዐ እስከ 6ዐ ያህል ከብቶች ታርደው እንዲከበር ይደረጋል፡፡ ቤንቾች በዓላትን፣ የዘመንና የወቅት አቆጣጠርን የጨረቃ መውጣትና መግባትን ተከትለው ከአዝመራ ወቅቶች ጋር በማዛመደ ያከብራል፡፡
ብሔረሰቡ ባህላዊ ቤቶችን ከእንጨት፣ ከጭቃ እና ከሣር የሚሠራ ሲሆን፤ጣራቸው በጭቃ የተሸፈነው ነው፡፡ የጎሣ መሪዎቹ ቤቶች ከፍታ ያላቸውና ሰፊ ናቸው፡፡ በብሔረሰቡ ከበቆሎ ወይም ከጤፍ የተሠራ ዳቦ፣ እንሰት(አምቾ)፣ ጎደሬ፣ እና የጎደሬ ገንፎ ይበላል፡፡ የቆጮ ቅቅል፣በቆሎ ተቆልቶ ከተፈጨ በኋላ የተዘጋጀ ጎመን ተጨምሮ በገንፎ መልክ ተዘጋጅቶ ይበላል፡፡
በብሔረሰቡ ወንዶች ሆዳቸውን በቀኝ እና በግራ ክንዳቸው አማካኝነት ቀጠን ያለ ‹‹ጋሱ›› የተባለ መስመር በመሥራት ያስውቡታል፡፡ ወንዶቹም ሆነ ሴቶቹ ለጉትቻ ጆሮአቸውን ይበሳሉ፡፡ አዛውንቶቹ ቁምጣ ሱሪ አንዳንዴም በላሌ፣ኩታ፣ ሹራብና ረጃጅም ልብሶችን ይለብሳሉ፡፡ ጦር መያዝም ልምዳቸው ነው፡፡
በብሔረሰቡ የለቅሶና የሀዘን ሥርዓት መሠረት ባለውቃቢ(ቃልቻ) ሲሞት አስከሬኑ ከመቀበሩ በፊት ውቃቢው በልጁ ወይም በዘመዱ ላይ እንዲወርድ በሚል በዋናው ቃልቻ ይለመናል፡፡ ባለአባቱ ወይም መሪ ሲሞት የሟች የቤተሰብ ቀብርን ከፈጸመ ከወር በኋላ መልዕክቱ ይተላለፋል፡፡ እየተደገሰ ሁለት ወር ይለቀሳል፡፡ ወጣት ሲሞት ለሳምንት ተለቅሶ በሦስተኛው ወሩ ልብሶቹ መቃብሩ ላይ ይጣላሉ፡፡ ንብረቱም እንዲወድም ይደረጋል፡፡
==ታዋቂ ሰዎች ==
{{መዋቅር-ብሔር}}
ቤንች የ[[ኢትዮጵያ]] ብሔር ነው።
[[መደብ:የኢትዮጵያ ብሔሮች]]
https://am.wikipedia.org/wiki/ቤንች
84s8ftaagdvy27lo1ocrqcyvxnmrsid
394795
394794
2026-08-17T12:52:35Z
~2026-45254-95
60166
/* ታሪክ */
394795
wikitext
text/x-wiki
==ቋንቋ==
የቤንች ብሔረሰብ ቋንቋ ‹‹[[ቤንችኛ]]›› ሲሆን ከምዕራብ ኦሞአዊ የቋንቋ ቤተሰብ ይመደባል። የብሔረሰቡ አባላት ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ [[አማርኛ]]፣ ካፊኖኖ እና [[ሸኮኛ]] ቋንቋዎችን ይናገራሉ።
==ሕዝብ ቁጥር ==
==መልክዓ ምድር ==
የቤንች ብሔረሰብ አባላት በዋናነነት በዞኑ በሰሜን ቤንች እና በደቡብ ቤንች፣በሸዋ ቤንች ወረዳዎች እንዲሁም በሸኮ እና ጉራፈርዳ ወረዳዎች ውስጥ ይኖራሉ፡፡ ከዞኑ ውጭም የብሔረሰቡ አባላት ኩታ ገጠም በሆኑት በከፋ ዞን በጨና እና ዳቻ ወረዳዎች፣ በሻካ ዞን በየኪ ወረዳ እንዲሁም በአዲስ አበባ ‹‹ጊሚራ›› ሰፈር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ይገኛሉ፡፡ ብሔረሰቡ የሚገኝበት አቀማመጥ ሜዳማ፣ ተራራማ እና ሸለቋማ ሲሆን፤ ደጋማ፣ ቆላማ እና ወይና ደጋ የአየር ንብረት አለው፡፡ የብሔረሰቡ ዋነኛ መተዳደሪያ ጥምር ግብርና ነው፡፡ ከተክሎች፣ ከሥራሥር፣ ከጥራጥሬ፣ ከቅመማቅመም ከአገዳ እህል የሚገኙ ምርቶች ያመርታል፡፡ ቡና ዋና የገቢ ምንጭ ሲሆን፤ ቅመማቅመም፣ ቆዳ እና ሌጦ ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ ናቸው፡፡
== ታሪክ ==
ቤንች ብሔረሰብ በቤንች ማጅ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ስድስት ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ነው፡፡ የብሔረሰቡ አሰያየም ‹‹ቤንችቲያት፣ሜርቲያት፣ሼይቲያት›› ከተባለው ጥንታዊ የብሔረሰቡ መሪ እንደተወለደ ይነገራል፡፡ ‹‹ታት›› የሚባለው ቃል ‹‹ጌታ›› ማለት ሲሆን ለብሔረሰቡና ለቋንቋው መጠሪያ ነው፡፡
በቤንች ብሔረሰብ በርካታ ጐሳዎች ቢገኙም ከምት፣ ቃም፣ ማንጃ(ባንድ) እና ማኖ(ፋቂ) ዋና ዋናዎቹ ናቸው በሐረሰቡ የራሱ የሆነ ባህላዊ አስተዳደር እና የዳኝነት ሥርዓት ያለው ሲሆን፤ ባህላዊ አስተዳደሩ የሥልጣን እርከን እና የሥራ ኃላፊነት የሚወሰነው በእርከኑ ባሉ ሽማግለዎችና በጎሳ መሪዎች ምርጫ ነው፡፡ ‹‹ከምት›› ከፍተኛ ከበሬታ የሚሰጠው መሪ ነው፡፡ ማንኛውንም ፖለቲካዊ ማኀበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮችን በበላይነት ይመራል፡፡ የባህላዊ አስተዳደሩ ቁንጮ ከእዚህ ጎሣ የሚሾም ሲሆን ‹ሜርቲያት› (ከምት) ባላባት ይባላል፡፡ የሚመረጠውም ‹‹ከዛግንድ›› ጎሳ ነው፡፡ የሥልጣን ሽግግሩም የዘር ሀረግን የተከተከለ ሲሆን የመሪዎቹ ወይም የ‹‹ቲያቶት›› ሥልጣን የሚተላለፈው ከ‹‹ቲያቶች›› የመጠሪያ ሚስት ለተወለደ የበኩር ልጅ ነው፡፡ መሪው ልጅ ሳይተካ ከሞተ ወንድሙ ሥልጣኑን ይወርሳል፡፡ ለ‹‹ቲያትነት›› የሚመረጠው ልጅ ወይም ወንድም በቂ ችሎታ ያለው እና ከሌለ ወገን ያልተከቀላቀለ ቤንች መሆን ይጠበቅበታል፡፡
ብሔረሰቡ ግጭቶችን የሚፈታበት የተለያዩ መንገዶች ያሉት ሲሆን፤ ግድያ ከተፈፀመ ወንጀሉ አፈፃፀም ከተጣራ በኋላ በሁለቱ ደመኞች ድንበር ላይ በሬ ታርዶ በደም ይታረቃሉ፡፡ ልጃገረድም ከገዳይ ወገን በካሳ ትሰጣለች፡፡ በብሔረሰቡ መዋሸት፣መሥረቅ፣ዝሙት መፈጸም አጥብቆ የተከለከለ ነው፡፡ ይህን ተግባር የፈጸመ ለቃልቻ ወይፈን ወይም ጊደር ይሰጣል፡፡ ከ1ዐ እስከ 3ዐ ጅራፍም ይገረፋል፤ በእግረሙቅ ይታሠራል፤ ለተወሰኑ ወራትም ለባላባቱ እንዲያደርስ ይደረጋል፡፡
በቤንች ብሔረሰብ የጋብቻ ሥርዓት በቤተሰብ ስምምነት፣በጠለፋ፣በማስኮብለል እና በውርስ ይፈጸማል፡፡ በብሔረሰቡ ሴት ልጅ 15 ዓመት ወንድ ልጅ ደግሞ 2ዐ ዓመት ሲሞላው የጋብቻ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ ባላባቱ እስከ 4ዐ ሚስቶችን ማግባት ሲችል አንጋፋዋ ሚስት ‹‹ጌን›› ትባላለች፡፡
በብሔረሰቡ ከወቅቶች ጋር ተያይዞ ምርት እንዲሰጥ፣ በሽታ እንዲጠፋ፣ ሰላም እንዲሰፍን በዓመት 3 ጊዜ የሚከበሩ በዓላት አሉ፡፡ በዓላቶቹ በቃልቻዎችና በባለአባቱ የሚመሩ ሲሆን፤ቦርዴ ተጠምቆ ልዩ ልዩ መልክ ያላቸው ዶሮዎች እና ከ5ዐ እስከ 6ዐ ያህል ከብቶች ታርደው እንዲከበር ይደረጋል፡፡ ቤንቾች በዓላትን፣ የዘመንና የወቅት አቆጣጠርን የጨረቃ መውጣትና መግባትን ተከትለው ከአዝመራ ወቅቶች ጋር በማዛመደ ያከብራል፡፡
ብሔረሰቡ ባህላዊ ቤቶችን ከእንጨት፣ ከጭቃ እና ከሣር የሚሠራ ሲሆን፤ጣራቸው በጭቃ የተሸፈነው ነው፡፡ የጎሣ መሪዎቹ ቤቶች ከፍታ ያላቸውና ሰፊ ናቸው፡፡ በብሔረሰቡ ከበቆሎ ወይም ከጤፍ የተሠራ ዳቦ፣ እንሰት(አምቾ)፣ ጎደሬ፣ እና የጎደሬ ገንፎ ይበላል፡፡ የቆጮ ቅቅል፣በቆሎ ተቆልቶ ከተፈጨ በኋላ የተዘጋጀ ጎመን ተጨምሮ በገንፎ መልክ ተዘጋጅቶ ይበላል፡፡
በብሔረሰቡ ወንዶች ሆዳቸውን በቀኝ እና በግራ ክንዳቸው አማካኝነት ቀጠን ያለ ‹‹ጋሱ›› የተባለ መስመር በመሥራት ያስውቡታል፡፡ ወንዶቹም ሆነ ሴቶቹ ለጉትቻ ጆሮአቸውን ይበሳሉ፡፡ አዛውንቶቹ ቁምጣ ሱሪ አንዳንዴም በላሌ፣ኩታ፣ ሹራብና ረጃጅም ልብሶችን ይለብሳሉ፡፡ ጦር መያዝም ልምዳቸው ነው፡፡
በብሔረሰቡ የለቅሶና የሀዘን ሥርዓት መሠረት ባለውቃቢ(ቃልቻ) ሲሞት አስከሬኑ ከመቀበሩ በፊት ውቃቢው በልጁ ወይም በዘመዱ ላይ እንዲወርድ በሚል በዋናው ቃልቻ ይለመናል፡፡ ባለአባቱ ወይም መሪ ሲሞት የሟች የቤተሰብ ቀብርን ከፈጸመ ከወር በኋላ መልዕክቱ ይተላለፋል፡፡ እየተደገሰ ሁለት ወር ይለቀሳል፡፡ ወጣት ሲሞት ለሳምንት ተለቅሶ በሦስተኛው ወሩ ልብሶቹ መቃብሩ ላይ ይጣላሉ፡፡ ንብረቱም እንዲወድም ይደረጋል፡፡
==ታዋቂ ሰዎች ==
{{መዋቅር-ብሔር}}
ቤንች የ[[ኢትዮጵያ]] ብሔር ነው።
[[መደብ:የኢትዮጵያ ብሔሮች]]
https://am.wikipedia.org/wiki/ቤንች
03yvgw1portyjkrwmthlxydt3nu2g5w